ኃይል አለ ከላይ
Hail Ale Kelay
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
ኃይል አለ ከላይ*2 የደከመ ሚበረታበት ያዘነ ሚጽናናበት የወደቀ ሚነሣበት የበረታው ሚቀጥልበት ኃይል የሌለውን ረዳኸው ምንኛ በጨለማ ቀኑ ሆነኸው ጓደኛ ደካማው ጀግኖ በክብር ቀጠለ ደግፎ የሚያቆም የእግዚአብሔር ኃይል አለ በመተማመን አንተን የጠበቀ አልቀረም ከቶ እንደ ወደቀ ኃይሉ ታድሶ እንደ ንሥር ድል ተቀዳጀ ቆመ በክብር ተስፋ ለቆረጠ ለወደቀ እምነቱ ራሱን ለቆጠረ እንደሆነ ከንቱ ኃይልህ ከጨለማ ያወጣና ነጥቆ በክብር ያቆመዋል ያኖራል አድምቆ ኃይል አለ ከላይ*2 የደከመ ሚበረታበት ያዘነ ሚጽናናበት የወደቀ ሚነሣበት የበረታው ሚቀጥልበት የተፍገመገመ ሊቆም ሚፍጨረጨር ብርታቱ ጌታ ነው የለም ከሱ በቀር በደስታ ይዘምራል ከሐዘኑ ተጽናንቶ ያከብረዋል አምላኩ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ኃይል አለ ከላይ*2 ሚበረታበት ሚጽናናበት ሚነሳበት ሚቀጥልበት

