Gubae

እንደገና

Endegena

ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017

የተዘጋ ምዕራፍ የተደመደመ አሁን የማይባል ያኔ ላይ የቆመ የፈረሰውን ቤት እንደገና ሠራ ተስፋ ፈነጠቀ አዲስ ብርሃን በራ ስንገዳገድ ሳለሁ በሕይወት ፈተና ጉልበቴ ዝሎብኝ በዝቶብኝ ፈተና ለነፍሴ ነግሬአት የመሞቴን ዜና ጌታ አቁሞኛል ዳግም እንደገና እንደገና የወደቀችውን እንደገና የዳዊትን ድንኳን እንደገና አድሶ ቀይሯል እንደገና የቀድሞ ታሪኳን እንደገና በእኔም ሕይወት ጌታ እንደገና ዘመናትን ቆጥሮ እንደገና በክብር አቁሞኛል እንደገና ታሪክን ቀይሮ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ በሸለቆ ውስጥ ተበታትነው የወደቁ ከሕያዋን ዓለም ፈፅመው የራቁ ሠራዊት ሆነው ዳግም ተነሡ ተአምርን ማድረግ ይችላል እርሱ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ የዘራሁትን ዘር በሐዘን በለቅሶ በደስታ አሳጨደኝ ምርኮዬን መልሶ የሐዘኔን ወራት ጌታ ተመልክቷል ምላሴ በእልልታ አፌ ሳቅ ተሞልቷል እንደገና ምስኪኑን ከትቢያ እንደገና አንሥተህ ከአፈር እንደገና ሞገሱ ሆንክለት እንደገና ክብርህን እንዲናገር እንደገና ማዳንህን ላውራ እንደገና ያ ሰው እኔ ነኝ እንደገና ሰው አይሆንም ሲሉ እንደገና ሰው ያደረከኝ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተጨመረልኝ እንደገና ክብር እንደገና ሞገስ እንደገና ጸጋ ተደረበልኝ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ነገርን ሁሉ የሚለውጠው እሱ የጠፋውን ያገኛል ፈልጎ ዳግም ይሠራዋል አዲስ አድርጎ አዲስ አርጎ አዲስ አርጎ ይሰራዋል ውብ አድርጎ ውብ አድርጎ

ቢንያም ዋለ · ሁሉም ዘማሪዎች