አይቀልብኝ
Aykelibigne
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
አይቀልብኝም አይቀልብኝም አይቀልብኝም የእሱ ውለታ ትውስ ይለኛል ትውስ ይለኛል ትውስ ይለኛል የእሱ ውለታ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ ሰንሰለቴን ጣለው እስራቴን ፈታ በጨነቀኝ ሰዓት ደረሰልኝ ጌታ ያደረገልኝን የማዳኑን እያየሁ ውለታውን እያሰብኩ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ ሰው ግራ ቢጋባ ቢሆንበት ትንግርት እርሱን በማምለኬ ቢበዛብኝ ትዝብት ከሆንኩለት በላይ ገና እሆናለሁ ውለታው በሕይወቴ በዝቶልኝ ስላየሁ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ መድኃኒት ሆነልኝ ሐዘኔን እንድረሳ በምሕረቱ ሻረው የኃጢአቴን ጠባሳ ኢየሱስ ባያገኘኝ እንዴት እሆን ነበር ባለውለታዬ ጌታ ስሙ ይክበር አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ ሕይወቴን ሲያስመርር ፈተናዬ በዝቶ ተስፋ ሲያስቆርጠኝ ሐዘኔ በርትቶ ምሕረቱ አከመኝ በፍቅሩ ተጽናናሁ የእርሱ መልካምነት መንገዴን አቀናው ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ የጌታ ውለታው ነው ሰው ያደረገኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ በጌታ ምሕረት ነው ዛሬን ያየሁኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ በጌታ ቸርነት ነው እዚህ የደረስኩኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ የኢየሱስ ፍቅር ነው በሕይወት ያኖረኝ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ

