Gubae

Kamlakachen Beqer

ብዙ ሙሉጌታ · ከአምላካችን በቀር ማነው አምላክ

ዘማሪ ፡ ብዙ ፡ ሙሉጌታ ርዕስ ፡ ከአምላካችን ፡ በቀር ጸሐፊ ፡ ሙሴ ካምላካችን ፡ በቀር ፡ ማነው ፡ አምላክ ከአለቱስ ፡ በቀር ፡ ማነው ፡ አለት እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ የድል ፡ ጋሻ ለክፉቀን ፡ ሆነልን ፡ መሸሻ ጌታችንን እኛ ፡ እናምነዋለን አሸንፎ ፡ ባይናችን ፡ ስላየን እየሱስን ፡ እኛ ፡ እናምነዋለን አሸንፎ ፡ ባይናችን ፡ ስላየን። ብዙዎች ፡ ተነሱ ፡ በእርሱ ፡ ላይ በስልጣን ፡ በሃይሉ ፡ በክብሩ ፡ ላይ አልጸኑም ፡ ወድቀዋል ፡ ተገርስሰው በሃያሉ ፡ ክንዱ ፡ ተመልሰው እኛም ፡ ታምነንበት ፡ በዚህ ፡ ጌታ እንዘላለን ፡ ዛሬ ፡ በደስታ። ኦሆ ... እኔ ፡ ማመልከው ኦሆ ... የምስግድለት ኦሆ ... የምገዛለት አምላኬ ፡ እግዚአብሄር ፡ ይሄ ፡ ነው። አማልክቶች ፡ አሉ ፡ በመደር ፡ ላይ ዝናቸው ፡ ለጥቂት ፡ ገኖ ፡ ሚታይ አይጸኑም ፡ ይወድቃሉ ፡ በአንድ ፡ አፍታ ሲነሳ ፡ በሃይሉ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ሲያሰግድ ፡ አየነው ፡ በአይናችን ሕዝቡን ፡ ያስከብራል ፡ አምላካችን። አባቶቻችንም ፡ ተማምነውት ነብያት ፡ ሐዋርያት ፡ ስሙን ፡ ጠሩት ሰማና ፡ ተገኝቶ ፡ አሳረፋቸው በጠላት ፡ ፊት ፡ መፈራት ፡ ሆናቸው ጥንት ፡ በደንቅ ፡ የሰራው ፡ ይሄ ፡ ጌታ በዙፋኑ ፡ አለ ፡ ሰይረታ። እንደ ፡ አምላካችን ፡ ማነው ፡ አለን በስሙ ፡ በክንዱ ፡ እኛ ፡ ፎከርን በመከራው ፡ ዘመን ፡ ተማመንነው ይሰራል ፡ ጌታችን ፡ ሃይለኛ ፡ ነው ለሁሉም ፡ ይሄን ፡ ክንዱን ፡ አሳያቸው እየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አሰኛቸው።

ብዙ ሙሉጌታ · ሁሉም ዘማሪዎች