Bezu Tetolegnal
ብዙ ሙሉጌታ · ከአምላካችን በቀር ማነው አምላክ
አዝ፦ ብዙ ፡ ትቶልኛል ፡ ብዙ ፡ እወደዋለሁ ብዙ ፡ እኔን ፡ ምሮኛል ፡ ብዙ ፡ አከብረዋለሁ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ በብዙ ፡ ዝማሬ ፡ ጌታን ፡ አከብራለሁ ገበናን ፡ ሰው ፡ መግለጥ ፡ ይወዳል ኃጢአትን ፡ መቼ ፡ ይቅር ፡ ይላል የእኔ ፡ ውድ ፡ ከዝህ ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ (፪×) ችሎኛል ፡ ሰዎች ፡ ይህንን ፡ ስሙኙ ፡ (፪×) አዝ፦ ስንቆም ፡ ሞገስ ፡ የሚያለብሰን ጻድቃኖች ፡ አድርጐ ፡ የቆጠረን ኢየሱስ ፡ ብዙ ፡ ትቶልናል ፡ (፪×) ምሕረት ፡ ዛሬም ፡ ያኖረናል ፡ (፪×) አዝ፦ ለመውገር ፡ ሁሉም ፡ ይቸኩላል ድንጋዩን ፡ በእጁ ፡ ተሸሟል ኢየሱስ ፡ የሰውን ፡ ድካም ፡ ያውቃል ፡ (፪×) ከአመድ ፡ ላይ ፡ ምስኪኑን ፡ ያነሳል ፡ (፪×) አዝ፦ ውለታው ፡ ለእኔ ፡ በዝቶብኛል ነውሬን ፡ ኢየሱስ ፡ ወስዶልኛል ውበቴ ፡ ድምቀቴ ፡ ሽቶዬ ፡ (፪×) ጠረኔ ፡ ሆነልኝ ፡ ጌታዬ ፡ (፪×) አዝ፦ ብዙ ፡ ትቶልኛል ፡ ብዙ ፡ እወደዋለሁ ብዙ ፡ እኔን ፡ ምሮኛል ፡ ብዙ ፡ አከብረዋለሁ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ ፡ (፬×) በብዙ ፡ ዝማሬ ፡ ጌታን ፡ አከብራለሁ ፡ (፬×)

