Amelkoyie
ብዙ ሙሉጌታ · ከአምላካችን በቀር ማነው አምላክ
አምልኮዬ ይገባሃል ላምልከው እያልኩኝ እወደዋለሁኝ የመስቀሉን ሚስጥር ፍቅር እያየሁኝ፥ ውለታው ስለ እኔ እጅግ በዝቷልና እኔም አበዛለው ለስሙ ምስጋና። የተነሱበትን ጥሎ አዋረዳቸው ስልጣኑን ቀምቶ ባዶ አደረጋቸው እነማን በርትተው እግዚአብሔርን ሻሩ እርሱ እኮ ይኖራል በነበረ ክብሩ። ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4) ፍቅጄ አመልከዋለው ወድጄ እንብረከካለው ልናገር ከምችለው በላይ ትልቅ ነው የክንዱ ስልጣን ገብቶኛል እዘምራለው ስልጣኑ ከማንም በላይ ነው። እንዴት ልናወጥ እንዴትስ ልፍራ እያየው እክንዱን ስራ ተደላድዬ ቆሚያለው ሃያሉን ክንዱን ይዣለው ሊሰራ እርሱ ሲነሳ እያየው ሁሉም ይታዘዛል። ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4) ሃያል ነን ጎበዝ ነን ያሉ በእርሱ ላይ ብዙ ፎከሩ ታገሰ ዘመን ሰጣቸው ታበዪ ክንዱ አጠፋቸው በዘመን በታሪክ የለም ስልጣኑ ፍጹም አልተሻረም። ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(8)

