Yibzalih Enji Misgana
ቤተልሔም ወልዴ · ትቼዋለሁ
ይብዛልህ እንጂ ምስጋና ይብዛልህ እንጂ አምልኮዬ ይብዛልህ እንጂ ክብር ይብዛልህ እንጂ ጌታዬ ማብዛት ለኔ ጥማቴ ነው ያለኝ የምሰጠው ይህን ነው በዘመኔ ሁሉ የማልመልሰው ውለታ አለብኝ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ለኔ ያደረገልኝ ብዘረዝረው ደግሞም ባወራው ከቁጥር ሁሉ በዛ እኔም በአለኝ ሀይሌ ምስጋና ለእሱ ላብዛ አዝ፡ ይብዛልህ እንጂ ምስጋና... አቤቱ አምላኬ ሆይ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ ክብርና ግርማ ብርሃንን እንደ ልብስ ለብሰህ በላይ በሰማይ ተውበህ በዙፋንህ ተቀምጠህ በፈጠርካቸው ፍጥረታት ሁሌ ትወደሳለህ አዝ፡ ይብዛልህ እንጂ ምስጋና... እግዚአብሔር በሰማይ የሚስተካከለው ማነው በዙሪያው ካሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው ስለዚህ በምስጋና ከፍ በል በእልልታ እጥፍ ድርብ ይሁንልህ ተመስገንልን ጌታ አዝ፡ ይብዛልህ እንጂ ምስጋና...

