Gubae

Tebeqagnaleh

ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት

ከሆነልኝ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ይልቅ ያረከው ፡ አንተ ፡ ሆንክልኝ ፡ ድንቅ (፪x) ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x) የከበደኝን ፡ ሁሉ ፡ አንተ ፡ አቀለልከው ፀሎቴንም ፡ እየሰማህ ፡ ጥያቄዬን ፡ መለስከው ለሰው ፡ ልጆች ፡ መልካምን ፡ በማድረግ ፡ ደስ ፡ ይልሃል ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ማንስ ፡ ይመስልሃል ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x) በዕድሌ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ በደረሰኝ ፡ እጣ ምታኖረኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ ባለጠጋ በክንዶችህ ፡ ተማምኜ ፡ በጥላህ ፡ አድራለሁ ጥጋቤ ፡ ነህ ፡ እርካታዬ ፡ አርፌብሃለሁ አዝ፦ ስለዚህ ፡ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ፡ ታስመካኛለህ (፪x) በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ሞልቶ ፡ የፈሰሰው (፪x) በውስጤ ፡ ያረከው ፡ የፍቅር ፡ እሳት ፡ ነው (፪x) ይህንን ፡ አይቼ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ (፪x) በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ አመሰግናለሁ (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፫x) ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ተባረክልኝ (፪x) ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ሰጠሁ ፡ እኔ ፡ እቆማለሁ (፪x) ቸርነት ፡ ምህረትህን ፡ ሁሌ ፡ እናገራለሁ (፪x) ድብቅ ፡ ጦር ፡ አንስተህ ፡ ጠላቴን ፡ መተሃል (፪x) ድል ፡ አድራጊው ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል (፪x) የእኔ ፡ ጌታ ፡ ተባረክልኝ (፫x) ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ተባረክልኝ (፪x) ታማኝነትህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ ቸርነትህን ፡ ዘለዓለም ፡ ዘምራለሁ (፪x) ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታዬ ሳከብርህ ፡ ያኔ ፡ ረካለሁ ፡ አምላኬ (፪x) ታማኝነትህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ ቸርነትህን ፡ ዘለዓለም ፡ ዘምራለሁ (፪x) ሌላማ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ ፡ ጌታዬ ሳከብርህ ፡ ያኔ ፡ ረካለሁ ፡ አምላኬ (፪x)

ቤተልሔም ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች