Selantema
ቤተልሔም ወልዴ · ቸር ነህ
ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሄር ፡ ኃያል ፡ ነህ ፡ ማንንም ፡ አትንቅም ደካማን ፡ በመጣል ፡ አንተ ፡ አትታወቅም ከጥንት ፡ የሰማነው ፡ በዓይናችን ፡ ያየነው ጻድቅነትና ፡ ሰውን ፡ መውደድህ ፡ ነው (፪x) አዝ ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) ጥንት ፡ አባቶቻችን ፡ ስራህን ፡ አወሩ ድንቅ ፡ ታምራትህን ፡ እየመሰከሩ ስራህ ፡ እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ (፪x) አዝ ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) የማወራው ፡ አለኝ ፡ የምመሰክረው ስለአንተ ፡ ምህረት ፡ ፍቅር ፡ የምናገረው ሥለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ሃጢአት ፡ ልጅህን ፡ ሰጥተሃል በእውነተኛ ፡ ፍቅርህ ፡ እኛን ፡ አድነሃል (፪x) ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ እኛን ፡ መውደድህ (፬x) ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እንላለን በላይ ፡ በላይ ፡ ምስጋና ፡ እንጨምራለን በላይ ፡ በላይ ፡ ክብርን እንጨምራለን ንገስ ፡ እንጂ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እንላለን በላይ ፡ በላይ ፡ ምስጋና ፡ እንጨምራለን በላይ ፡ በላይ ፡ ዝማሬ ፡ እንጨምራለን ልነሳና ፡ ልነሳና ላክብርህ ፡ ምክንያት ፡ አለኝ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ምክንያት ፡ አለኝ ፡ ክበር (፫x) ምስጋና ፡ ላንተ ፡ ነው ክብርም ፡ ላንተ ፡ ነው አምልኮ ፡ ላንተ ፡ ነው ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ነው ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃሃ (፪x) ውዳሴም ፡ ላንተ ፡ ነው ቅዳሴም ፡ ላንተ ፡ ነው ጭብጨባም ፡ ላንተ ፡ ነው እልልታም ፡ ላንተ ፡ ነው ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃሃ (፪x))

