Qedus
ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት
ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር (፪x) በታላቅ ፡ ብርሃን ፡ በክብር ፡ ያለህ ግርማህ ፡ አስፈሪ ፡ መሳይ ፡ የሌለህ ፍጥረት ፡ በፊትህ ፡ ይንቀጠቀጣል ክብርህን ፡ አይቶ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይቆማል? ቅዱስ (፫x) ፡ እግዚአብሔር (፪x) በፈቃዴ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ (፬x) አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ክበር ፡ ጌታ (፬x) ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ንገሥ ፡ ጌታ (፬x) ስለአንተ ፡ በየዕለቱ ፡ መደነቅ ፡ ሞልቶኛል ዛሬም ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አምልኪው ፡ ይለኛል ለምን ፡ እንደምኖር ፡ ምክኒያቱ ፡ ገብቶኛል አንተን ፡ ለማምለክ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ተስማምቶኛል በመፍራት ፡ በመንቀጥቀጥ ፡ በፊትህ ፡ እቀርባለሁ ክብር ፡ ለሚገባህ ፡ ለአንተ ፡ ክብርን ፡ እሰጣለሁ አምላኬ ፡ ይገባሃል ፡ ክብር አምላኬ ፡ ይገባሃል አምላኬ ፡ ይገባሃል ፡ ስግደት አምላኬ ፡ ይገባሃል (፪x) አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ክበር ፡ ጌታ (፬x) ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ንገሥ፡ ጌታ (፬x) አምላክ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ክበር ፡ ጌታ (፬x) ንጉሥ ፡ ስለሆንክ ፡ ስለሚገባህ ንገሥ ፡ ጌታ (፬x)

