ቃልህን ወደድኩት
Qalehen Wededkut
ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት
አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x) ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x) ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ቃሉ ፡ የነጠረ ፡ ነው ለሚታመኑበት ፡ እርሱ ፡ ጋሻ ፡ ነው ለቃልህ ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ እገዛለሁ ሁኚ ፡ ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ዛሬም ፡ እሆናለሁ ያፅናናኝን ፡ የደረሰልኝን በመንገዴ ፡ ሁሌ ፡ የሚመራኝን ሕይወቴንም ፡ ለቀየረልኝ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ሁሌ ፡ አስተማማኝ አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x) ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x) ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x) ከአፍህ ፡ የሚወጣው ፡ ሕያው ፡ የአንተ ፡ ቃል መሻት ፡ ግን ፡ ወደ ፡ እኛ ፡ ስቦ ፡ ያመጣል ያድናል ፡ ይገላል ፡ ይተክላል ፡ ይነቅላል እርሱ ፡ ያለው ፡ ብቻ ፡ በእርግጥም ፡ ይሆናል ሳር ፡ ይደርቃል ፡ አበባው ፡ ይረግፋል በምድር ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይለዋወጣል ዘመን ፡ ጊዜ ፡ የማይለዋውጠው የአምላኬ ፡ ቃል ፡ ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ነው አዝ፦ ብዙ ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው በቃልህም ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ መተኪያና ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x) ቃልህን ፡ እወደዋለሁ (፪x) ድምጽህን ፡ እወደዋለሁ (፪x)

