Menoriyayie
ቤተልሔም ወልዴ · ቸር ነህ
ዘማሪ ፡ ቤቴልሔም ፡ ወልዴ ርዕስ ፡ መኖሪያዬ አልበም ፡ ቸር ፡ ነህ አዝ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል ፡ እፎይ እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቻለሁ (፪x) ወዳጅ ፡ እንደሌላቸው ፡ አልተዋችሁም ፡ አልረሳችሁም ብለህ ፡ ተናግረሃል ፡ ያልከውን ፡ ልትፈጽም ፡ አንተ ፡ ሄደሃል አንተ ፡ ባለህበት ፡ እኛን ፡ ልታኖረን ፡ ልታሳርፈን በቅርብ ፡ ትመጣለህ ፡ አሜን ፡ ጌታችን ፡ ቶሎ ፡ ናልን አዝ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል ፡ እፎይ እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቻለሁ (፪x) በአባቴ ፡ ቤት ፡ ብዙ ፡ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ማረፊያ ፡ አለ ተመለሱ ፡ ይብቃ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እረፍቱ ፡ ግቡ ፡ ትላለህ ሰምቶ ፡ ላመነበት ፡ መኖሪያ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ማረፊያ ፡ አንተ ፡ ነህ ነፍስን ፡ ከሚያጐድል ፡ ትጠብቃለህ ፡ ትጋርዳለህ አዝ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ መኖሪያዬ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል ፡ እፎይ እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አንተን ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

