Gubae

Lenie Gen

ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት

የሚሰማ ፡ ግን ፡ በእርጋታ ፡ ይቀመጣል ከመከራ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሥጋት ፡ ያርፋል ጌታዬ ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x) ብለሃል ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x) አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x) የሚያስፈልገው ፡ ጥቂት ፡ አንድ ፡ ነው (፪x) በእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኖ ፡ አንተን ፡ ማድመጥ ፡ ነው (፪x) ይህን ፡ ተረዳሁ ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x) ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ አደምጥሃለሁ (፪x) አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x) ከዝማሬዬ ፡ ይልቅ ፡ ኑሮዬ ፡ ያክብርህ (፪x) በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ ስንቱን ፡ ላስጠራልህ (፪x) ከአገልግሎቴ ፡ ይልቅ ፡ ሕይወቴ ፡ ያማረ ፡ ይሁን (፪x) አንተ ፡ እንደምትወደው ፡ እንደፈቀድክ ፡ ይሁን (፪x) አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x) ጌታዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ (፪x) ፊትህንም ፡ ማየት ፡ እጅግ ፡ ናፍቃለሁ (፪x) የሚረዳኝ ፡ ፀጋ ፡ ከአንተ ፡ ፈልጋለሁ (፪x) ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እቀርባለሁ (፪x) የሚሰማ ፡ ግን ፡ በእርጋታ ፡ ይቀመጣል ከመከራ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሥጋት ፡ ያርፋል ጌታዬ ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x) ብለሃል ፡ እሰማሃለሁ ፡ ከጭንቀት ፡ ከሃዘን ፡ አርፋለሁ (፪x) አዝ፦ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ጌታዬ ፡ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ለእኔ ፡ ግን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መቅረብ ፡ ይሻለኛል (፫x)

ቤተልሔም ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች