Endewededkegn Aweku
ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት
ምሥጋናን ፡ የሚሰዋ ፡ ያከብረኛል ፡ ያከብረኛል ፡ ብለሃል እሰዋለሁ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው እሰዋለሁ ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x) ምሥጋናን ፡ በአፌ ፡ የጨመርክ ምሬትን ፡ ከእኔ ፡ ያስወገድክ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህና ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና ይገባሃልና ፡ አሜን ፡ ይገባሃልና እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን ከዙፋንህ ፡ ስርም ፡ እንሰግድልሃለን እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ እንሰግድልሃለን ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ጌታዬ ሞገስ ፡ ያግኝ ፡ ምሥጋናዬ ሳከብርህ ፡ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለኛል እረካለሁ ፡ ክብርህ ፡ ያጠግበኛል ክብርህ ፡ ያጠግበኛል ፡ አሜን ፡ ክብርህ ፡ ያጠግበኛል እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን ከዙፋንህ ፡ ስርም ፡ እንሰግድልሃለን እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ እንሰግድልሃለን ድል ፡ በመንሳቱ ፡ ለሚያዞረኝ በጠላቶቼ ፡ ዕራስ ፡ ላይ ፡ ላቆመኝ እዘምራለሁ ፡ ለጌታ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ እዘምራለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ እዘምራለሁ ፡ ኦሆ ያስጨናቂውን ፡ ዘንድ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበርከው ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ ከላዬ ፡ አስወገድከው ሁሌ ፡ እደነቃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ በማዳንህ ባለህ ፡ ምሥጋና ፡ ላይ ፡ ሌላም ፡ ልጨምርልህ (፪x) ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ ጣላቴ ፡ ይዞራል ፡ የሚውጠው ፡ ፈልጐ ምንም ፡ ላይሞላለት ፡ ሁሌ ፡ መናውን ፡ ቀርቶ እኔን ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ከድል ፡ ድል ፡ ያዞረኛል ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ ጌታዬ ፡ አስረግጦኛል (፪x) ጠላቴ ፡ ዕልል ፡ አይልብኝምና እንደወደድከኝ ፡ አወቅሁ እንደመረጥከኝ ፡ አወቅሁ (፪x) በእኔ ፡ ድንኳን ፡ ዕልልታ ፡ ይሰማዋል ፡ ዝማሬ ፡ ይሰማዋል የወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል የመረጠኝ ፡ እርሱ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል የማንም ፡ ባለዕዳ ፡ ያልሆነው ፡ እግዚአብሔር አፈራረሰና ፡ የጠላቶቼን ፡ ምክር አዳዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በአፌ ፡ ውስጥ ፡ ሲጨምር የነፍሴ ፡ ቅኝቷ ፡ ሁሌ ፡ ክብር ፡ ክብር (፪x) ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ ክበር ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር ፤ ንገሥ ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር (፪x) እስማማለሁ ፡ እኔም ፡ እጨምራለሁ (፬x) ክበር ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር ፤ ንገሥ ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር (፪x) እስማማለሁ ፡ እኔም ፡ እጨምራለሁ (፬x)

