Belielitem
ቤተልሔም ወልዴ · ቃልህን ወደድኩት
በሌሊትም ፡ ከልቤ ፡ ጋር ፡ ተጫወትኩኝ ነፍሴንም ፡ አነቃቃኋት ፡ ጌታን ፡ አሰብኩኝ እርሱን ፡ ሳስብ ፡ ልቤ ፡ በደስታ ፡ ሁሌ ፡ ይሞላል ያስጨነቀኝንም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ይጥላል እግዚአብሔርን ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለኝ እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስ ፡ አለኝ እርሱን ፡ ተመልከቱ ፡ ያበራላችኋል (፪x) የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x) ወደ ፡ እርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ያበራላችኋል የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x) ለተጨነቀ ፡ ሰው ፡ ጨለማ ፡ አይሆንም ፡ ብሏል በእውነት ፡ ለሚታመኑት ፡ ልቡ ፡ ይራራል አሁንም ፡ ተስፋዬም ፡ ትዕግሥቴም ፡ በእርሱ ፡ ነው በዘመኔ ፡ እያሰብኩት ፡ እደሰታለሁ እግዚአብሔርን ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለኝ እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስ ፡ አለኝ እርሱን ፡ ተመልከቱ ፡ ያበራላችኋል (፪x) የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x) ወደ ፡ እርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ያበራላችኋል የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x) ስትፈለግ ፡ የምትገኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ምታጽናና ፡ ምትደግፍ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ በብርሃንህ ፡ ብርሃን ፡ እንዳይ ፡ አደረከኝ በቀረብኩህ ፡ ቁጥር ፡ ጌታ ፡ አበራህልኝ አንተ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ እታመንሃለሁ ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ ላይ ፡ ይኸው ፡ አንስቻለሁ አንተ ፡ ብቻህን ፡ በቂ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x) አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x) አንተ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ እታመንሃለሁ ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ ላይ ፡ ይኸው ፡ አንስቻለሁ አንተ ፡ ብቻህን ፡ በቂ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x) አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x)

