Balewuletayie
ቤተልሔም ወልዴ · ቸር ነህ
ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ ቅዱስ ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ ውለታህን ፡ አስታውሰዋለሁ (፪x) ለኔ ፡ ነው ፡ መንከራተትህ መስቀል ፡ ተሸክመህ ፡ መውረድህ ለኔ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ያላበህ ፍቅር ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ ያስጨነቀህ ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ... ከአብ ፡ ዘንድ ፡ ለኔ ፡ የተሰጠ ትልቁ ፡ ስጦታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ይህ ፡ ሚስጥር ፡ ለኔ ፡ ተገልጾል መዳን ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሆኖልኛል ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ... ልከፍለው ፡ እማልችል ፡ ውለታ ያኔ ፡ ያረከውን ፡ በጐልጐታ ምስጋናን ፡ ሙገሳን ፡ ይዤ ላክብርህ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ፈቅጄም ፡ አመልክሃለሁ ውለታህን ፡ አስታውሳለሁ ወድጄም ፡ አመልክሃለሁ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ...

