Meheretun Asebie
ቤተልሔም ተዘራ · ተፈጸመ
ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x) ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ፡ ድንቅ ፡ ነው (፫x) አዝ፦ ምሕረቱን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ፍቅሩ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አሃ ፍቅሩን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ባርኮቱ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ለካ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አመስግኜው ፡ ልርካ (፬x) አልጠፋብሽ ፡ ያለኝ ፡ ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ የእግዚአብሔርስ ፡ ፍቅር አሳዳጊነቱ ፡ አባትነቱ ፡ ከህይወቴ ፡ ጅምር ትዝታ ፡ አይደለም ፡ እያነሳሁ ፡ ምተርክለት በርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ እስከ ፡ አሁኗ ፡ ድረስ ፡ ያለሁት (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ሰው ፡ ወዳድነትህ ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት የፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት እሩህሩህነትህ ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት (፪x) አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ ውለታውን ፡ አስቤ ፡ ልቆጥር ጥፍት ፡ ይለኛል ፡ ከየት ፡ ተነስቼ ፡ እንደምጀምር ይህ ፡ እንኳን ፡ ቢረዳኝ ፡ ቢነግርልኝ ውስጤን ፡ ቢገልጸው እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ብዬ ፡ ልደምድመው (፪x) እንደእግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት እንደእሱ ፡ የለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት ቢፈለግ ፡ ዘላለም ፡ አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት (፪x) አዝ፦ ምሕረቱን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ፍቅሩ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አሃ ፍቅሩን ፡ አስቤ ፡ አቤት ፡ ስል ፡ ባርኮቱ ፡ አለ ፡ ለካ ፡ አለ ፡ ለካ ኧረ ፡ እንዴት ፡ አመስግኜው ፡ ልርካ(፬x)

