Gubae

Beyemaledaw

ቤተልሔም ተዘራ · ዕድሜዬ በቤትህ ይለቅ

ስለ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት በየማለዳው ፡ የምረዳው ዕለት ፡ በዕለት ፡ ሚታይ ፡ እውነት (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x) ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x) ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x) ያለጠፋሁት ፡ በምን ፡ ምክንያት ከቦኝ ፡ እንጂ ፡ የአንተ ፡ ምህረት እያለፈ ፡ እየተከተለኝ ክፉዉን ፡ ሁሉ ፡ ጥግ ፡ አስያዘልኝ የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ ደግነትህን ፡ ይመስክር በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ የሕይወቱ ፡ መስመር (፪x) ቸር ባትሆን ባለ ምህረት እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (፪x) ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑህ ለሚወዱህም ቸር ለሚያምኑብህ (፪x) አልጣሉኝም ፡ ደጋግ ፡ እጆችህ ፍቅር ፡ ናቸው ፡ ዛሬም ፡ ዓይኖችህ ለዘለዓለም ፡ ቤትህ ፡ እኖራለሁ ወደኸኛል ፡ እስከ ፡ መጨረሻው የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ ደግነትህን ይመስክር በአንተ የቀናለት አሃ የሕይወቱ መስመር (፪x) ቸር ፡ ባትሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x) ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑህ ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበህ (፪x)

ቤተልሔም ተዘራ · ሁሉም ዘማሪዎች