Yibzalegn Metazezie
በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር
ግራ ቀኜን ላንተ ትጉ አድርገው ቀን ሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ ኢያኤል ያቺ ሴት ግራዋም ቀኟም ታዛዥ በድንኳን ከሚኖሩ ከሴቶች ይልቅ የተለየች ውሀ ለለመነ ወተት ሰጪ በከበረ ዳካ ሲሳራን የዘረረችው በእግሯ ስር አጋድማ ግራዋን ለካስማ ቀኝ እጇን ለመዶሻ በጥበብ የተሞላች ጠላትን የዘረረች የሆነች ታታሪ ለመንግስትህ ሰሪ የሆነች ሰራተኛ ለስራህ የማትተኛ ግራ ቀኜን ላንተ ትጉ አድርገው ቀን ሳለ ልሩጥህ መንግስትህን ላስፋው ደጆቼ ተከፍተው ብርሃኔም በርቶ የመንግስትህ ጉዳይ ያጥምደኝ በዝቶ ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ በችግር በመከራ በፅናት ወንጌል ሰባኪ በድንጋይ ተወግሮ ማልዶ ለወንጌል ዘማች ግርፋት ደዌ ማያስቆመው በዕፉኝት መነደፍ እለት እለት ሚያሳስበው የመንግስትህ መስፋት ሁልጊዜ ደስ የሚለው ታስሮ እንኳን የማይከፋው እንደ ጳውሎስ የጀገነ እስከ ሞት የቆረጠ የሆነ ሰራተኛ ለወንጌል የማይተኛ የሆነ ታታሪ ለመንግስትህ ሎሌ በዚህች አጭር እድሜ መላኬን ዘንግቼ ለራሴ ጉዳይ እንዳይሆን ሩጫዬ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ ከለየኝ የኔ ብሎ እሮጣለሁኝ ከስጋ ከደም አልማከርም *2 ይብዛልኝ መታዘዜ ይብዛልኝ ላንተ መሮጤ ይብዛልኝ የመንግስትህ ጉዳይ ይክበደኝ ከሌላው በላይ

