Etebiqehalehu
በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር
ሆድ ሲብሰኝ ደግሞ ስትዘገይ የቀረህብኝ ሲመስለኝ ነብስ ስጋዬ ሲጨነቅ ለመቆም ስዝል ሲደክመኝ ብርታቴም ሲከዳኝ ስዳከም ጥያቄ ነብሴን ሲከባት መልስ እንኳን ባይኖረኝ ለነፍሴ እንዳንተ ሚሆን ማን አላት የተማመንኩብህ አለ ያልኩህ ጌታ አንተን ተማምኜ የባሰ ቢመጣ ታምንሃለች ነፍሴ እርምጃ ቀርቶኝ ለሞት እጠብቅሃለሁ እስከመጨረሻ እስትንፍስ ይስሀቅ ጠብቆህ የል በጌራራ ምንም በሌለበት ስፍራ ካንተ ጋር እሆናለሁ ስትለው አንተን አምኖ እንደዘራ መቼ ቀረ ታዲያ በባዶ አንተን ጠብቆ ጠብቆ አጭዶ የለም ወይ መቶ እጥፍ ምድረበዳ ላይ ዘርቶ የተማመንኩብህ አለ ያልኩህ ጌታ አንተን ተማምኜ የባሰ ቢመጣ ታምንሃለች ነፍሴ እርምጃ ቀርቶኝ ለሞት እጠብቅሃለሁ እስከመጨረሻ እስትንፍስ አብርሀምም ወጣ ከካራን የተገለጠለትን አምኖ ድንኳኑን ተከለ ምድረበዳ እንደመፃተኛ ሆኖ ሙት እንኳን ከሆነው ከስጋው ከ ደከመ ጉልበቱ አምኖህ የለም ወይ ያለምክንያት የሚያስክድ ሰበቡን ትቶ የኔና ያንተ መዋደድ የኔና ያንተ ቁርኝት ከምክንያት ከሰበብ አልፎ ሆኖ የል ያለልክ ያለ ምስክር ማስረጃ እንዳመነህ እንደ አብርሐም የኔም ልብ በአንተ ላይ እንደዛው ፀንቶአል አመንኩህ ከነጥያቄዬ አመንኩህ በጎደለኝ አመንኩህ ቀረኝ ከምለው አመንኩህ እኔ ወደድኩህ

