Gubae

Bemejemeriya

በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር

በመጀመሪያ ቃል ነበር ሌላ አልነበረም ፍጥረት ሳይፈጠር ነበረ ተብሎ እንጂ ጅማሬህን አውቆ ማን ይናገራል ስላንተ ሚያወጋ ከአንተ ቀድሞ የኖረ አልኖረም… የህይወት መገኛ የፍጥረት ምንጭ ነህ አልኖረም… ህይወት ባንተ ይገኛል ለሰው ብርሃን ሆኖአል ፍጥረታት በቃል ሳይፈጠሩም በፊት ቃል እግዚአብሔር ነበር የሚኖር ዘላለም ቃልም ስጋ ሆኖ በኛ ዘንድ ያደረው ዓለማት ሳይኖሩ እርሱ ያው እሱ ነው በመጀመሪያ ቃል ነበር ሌላ አልነበረም ፍጥረት ሳይፈጠር ነበረ ተብሎ እንጂ ጅማሬህን አውቆ ማን ይናገራል ስላንተ ሚያወጋ ከአንተ ቀድሞ የኖረ አልኖረም… የህይወት መገኛ የፍጥረት ምንጭ ነህ አልኖረም… ህይወት ባንተ ይገኛል ለሰው ብርሃን ሆኖአል አትለካም ከቶ በሰዎች መለኪያ እልፍ ቃላት በዝቶ አንተን አያብራራ እርጅና ተጭኖህ ደግፉኝ አትልም ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም አለህ ፍጥረት ይኖራል ባንተ.. አያኖርህ አንተን ህይወት ይኖራል ባንተ አያኖርህ አንተን የሁሉ መገኛ አንተ የሁሉ ጅምር አንተ በጊዜ አትለካም አንተ ዘመን አይሽርህም አንተን

በረከት ለማ · ሁሉም ዘማሪዎች