Gubae

Ale Yemigebaw

በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር

ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ ጸሎት ልመናን አቀረበ በእንባ ምን አለ የማይገባው ሰው ሆኖ ሰውን ስላየው / ማይረዳው ትሁት ሆኖ በመታዘዝ ወዶን የል እስከሞት ድረስ አለ የሚገባው አለ ሰው የሆነ አለ ሚራራልን አለ የተፈተነ አለ በመስቀል ሞት አለ ህመም ያወቀ አለ ደም እስኪያልበው አለ ጭንቀትን ያየ ወደሰማይ ያረገው ታላቅ ሊቀ ካህን የራሱን ደም ይዞ ገባ አስታረቀን ከአብ ጋር የዘላለም ቤዛነትን ሊያስገኝልን በደሙ እግዚአብሔርን እንድናመልክ ህሊናችንን አጠበው አለ የሚገባው አለ ሰው የሆነ አለ ሚራራልን አለ የተፈተነ አለ በመስቀል ሞት አለ ህመም ያወቀ አለ ደም እስኪያልበው አለ ጭንቀትን ያየ ይራራል ቢባል በሱ ያምራል ይረዳል ቢባል ከሱ ማን ይልቃል በመከራ ተፈትኖ መታዘዝን ተምሮአል *2 እግዲህ ምህረትን እንድንቀበል እንዲያግዘን ጸጋው በሚያስፈልገን ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቀርባለን ሲደክመን አግዘን እንላለን

በረከት ለማ · ሁሉም ዘማሪዎች