Gubae

ወዶ ዘማች

Wedo Zemach

በረከት አለሙ · ወዶ ዘማች

ከተሸሸኩበት ፡ መንደሬ መጣ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ሰፈሬ ጠራኝ ፡ ቀርቦ ፡ በቁልምጫው ሊያስገባኝ ፡ ወደ ፡ ጉያው የወዳጄ ፡ የአምላኬ    ጥሪው ፡ ደርሶኛል    ምን ፡ አደርጋለሁ    ቀሪው ፡ ዘመኔን ፡ ሰጥቼዋለሁ    ይስራበት ፡ ይክበርበት    ያለው ፡ አላማ ፡ ፈቃድ ፡ ሀሳቡ    ይጠቅለል ፡ በእኔ ፡ ይድረስ ፡ ከግቡ ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) (፪x) መገለጫው ፡ ነው ፡ መገለጫው    ለሰማይ ፡ ወኪል ፡ የምድር ፡ ጨው    የምድርን ፡ ክፋት    መርገም ፡ ሰባሪ    የሰላም ፡ ዘማች ፡ ለሰማይ ፡ ጥሪ (፪x) ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ (፪x) ማያንገራግረው ፡ ማያመቻምቸው    ትዳር ፡ ባለበት ፡ ሰፈር    ራሱን ፡ የማይጠምደው    ጠሪውን ፡ ሲያስደስተው    ሲገኝ ፡ በጸና ፡ እምነቱ    ማረጉ ፡ ነው ፡ በላዩ    ሚታየው ፡ ሽልማቱ (፪x) ወዶ ፡ ዘማች ፡ ወዶ ፡ ዘማች ለወንጌሉ ፡ ወዶ ፡ ዘማች ፈቅዶ ፡ ዘማች ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች ለዚህ ፡ ጥሪ ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች ማነው (ወዶ ፡ ዘማች)    ማነው (ለዚህ ፡ ጥሪ)    ማነው (ራሱን ፡ ሰቶ)    ማነው (ጌታውን ፡ አስጠሪ)    ማነው (እኔ ፡ ነኝ)    ማነው (እኔ ፡ ነኝ)    ማነው (እኔ ፡ ነኛ)    ማነው (ለወንጌሉ)    ማነው (ዘማች ፡ አርበኛ) ማነው (፬x) ማነው

በረከት አለሙ · ሁሉም ዘማሪዎች