Gubae

Shelematie

በረከት አለሙ · ወዶ ዘማች

ጌጤ ፡ ወርቄ ፡ ውበቴ ፡ ደም ፡ ግባቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)                        ከ ፡ ነገድ ፡ ቋንቋ ፡ በ ፡ ልጁ ፡ የዋጀኝ               ወደከበረ ፡ መንግስቱ ፡ ያፈለሰኝ               ከላይ ፡ ሲመጣ ፡ የተቀበልኩት ፡ ስጦታዬ               ወራሽ ፡ አረገኝ ፡ የ ፡ እርስቱ ፡ ተካፋይ (5) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)                     እኔን ፡ ለማድረግ ፡ ባለጠጋ ፡ ሆነህ ፡ ባዶ              ውበት ፡ ሊሰጠኝ ፡ በኔ ፡ ምትክ ፡ ተሰቃይቶ              በሰማያዊ ፡ በረከቱ ፡ ባረከኝ              በ ፡ ጸጋው ፡ ሙላት ፡ በ ፡ መንፈሱ ፡ ከበበኝ (5) ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)                     የታረደው ፡ ኢየሱስ ፡ ፋሲካዬ              የሞትን ፡ ጣር ፡ ገፈፈልኝ ፡ ከላዬ              ዳግም ፡ ህይወት ፡ አገኘሁ ፡ ታደስኩኝ              የ ፡ እግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ በመሆን ፡ ጸደኩኝ                        አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ጸደኩኝ (2)                        አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከፍ ፡ አልኩኝ (2)                        አ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ከበርኩኝ (2)                        አ ፡ ሃ ፡ ሃ (2) ማንም ፡ የተጠማ ፡ ይምጣና ከ ፡ ህይወት ፡ ውሃ ፡ ይጠጣና በ ፡ ሰላም ፡ ይኑር ፡ በ ፡ እርጋታ ብሎ ፡ ተናግሮአል ፡ ይሄ ፡ ጌታ እኔም ፡ ሰማሁት ፡ ወዳጄን የ ፡ ህይወት ፡ መንገድ ፡ መሪዬን ውጬዋለሁኝ ፡ መድሃኒቴን አትርፌአታለሁ ፡ ይህች ፡ ነፍሴን ሽልማቴ ፡ ሽልማቴ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሽልማቴ (2)

በረከት አለሙ · ሁሉም ዘማሪዎች