የሕይወት ውኃ
Yehiwot Wiha
አዜብ ኃይሉ · ሕያው አምላክ ነህ · 2024
የእኔ ፡ ሙግት ፡ የእኔ ፡ ክርክር ማንነቱን ፡ ሳልውቀው ፡ ነበር የሕይወቴ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ እንዳለ ያስተዋልኩት ፡ ዘግይቼ ፡ ነበር ጉዴን ፡ ውስጤን ፡ አውቆ ፡ የነገረኝ ወደ ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የመለሰኝ ለካስ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ኢኢየሱስ ፡ ነው ማን ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ የሕይወት ፡ ውኃት ፡ ሰጣለህ አንተ ፡ የምትሰጠውን ፡ የሚጠጣ ዳግም ፡ እንዳይጠማው ፡ ታረካለህ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ነህ ከያዕቆብ ፡ ጉድጓዶች ፡ የመነጨ ፡ ውሃ ከቶ ፡ አያሻግርም ፡ የዓለምን ፡ በረሃ አንተ ፡ ግን ፡ ኢኢየሱስ ፡ የምትሰጠው ለዘላለም ፡ ሕይወት ፡ የሚያዘልቅ ፡ ነው የዘላለም ፡ ነው ማን ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ የሕይወት ፡ ውኃት ፡ ሰጣለህ አንተ ፡ የምትሰጠውን ፡ የሚጠጣ ዳግም ፡ እንዳይጠማው ፡ ታረካለህ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ነህ ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ የሕይወት ፡ እንጀራ ዘላለም ፡ እንድኖር ፡ ከእርሱ ፡ ስበላ ወዶ ፡ በፈቃዱ ፡ ራሱን ፡ አቀረበ ደግ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ ፡ ለነፍሴ ፡ ያሰበ ለነፍሴ ፡ ያሰበ ከእንግዲህ ፡ ከአንተ ፡ ወደት ፡ እሄዳለሁ ከአንተ ፡ ወዴት የሕይወት ፡ ውኃ ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ ከአንተ ፡ ወዴት እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ከአንተ ፡ ወዴት የሕይወት ፡ ቃል ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ ከአንተ ፡ ወዴት ከእንግዲህማ ፡ ከአንተ ፡ ወደት ፡ እሄዳለሁ ከአንተ ፡ ወዴት የሕይወት ፡ ውኃ ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ ከአንተ ፡ ወዴት እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ከአንተ ፡ ወዴት የሕይወት ፡ ቃል ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ ከአንተ ፡ ወዴት

