ተነሳ
Tenesa
አዜብ ኃይሉ · በመጀመሪያ እግዚአብሔር · 2017
አላመልክም ፡ ሞቶ ፡ የቀረ ፡ የተነሳውን ፡ ነው ፡ እንጂ እውነት ፡ ነው ፡ ሞቶ ፡ ነበር ፡ ግን ፡ ተነስቷል ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ገደልነው ፡ ብለው ፡ ቢያወሩ ፡ አኑረነዋል ፡ ከመቃብር በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳ ፡ በትንሳኤው ፡ ታላቅ ፡ ክብር ተነሳ ፡ ሞት ፡ ተሸነፈ ፡ ተነሳ ፡ ኃይል ፡ አጣ ፡ ከቶ ተነሳ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ ተነሳ ፡ መቼ ፡ በርትቶ ተነሳ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ ፡ ተነሳ ፡ ወጣ ፡ ወደላይ ተነሳ ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ተነሳ ፡ ከብሯል ፡ በሰማይ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ በትንሳኤው ፡ ቀን ፡ ማለዳ ፡ ባዶ ፡ ነበር ፡ መቃብሩ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ እንደወጣ ፡ መላእክቱ ፡ መሰከሩ ሃዋርያቱም ፡ አስታወሱ ፡ የተሰጣቸውን ፡ ተስፋ ጊታቸው ፡ ሞቶ ፡ እንደማይቀር ፡ እንደ ፡ ሌሎች ፡ እንደማይጠፋ ተነስቷል ፡ ሞት ፡ ተሸነፈ ፡ ተነስቷል ፡ ኃይል ፡ አጣ ፡ ከቶ ተነስቷል ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ ተነስቷል ፡ መቼ ፡ በርትቶ ተነስቷል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ ፡ ተነስቷል ፡ ወጣ ፡ ወደላይ ተነስቷል ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ተነስቷል ፡ ከብሯል ፡ በሰማይ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ የትንሳኤው ፡ ምስክሮች ፡ አይተውታል ፡ በዓይናቸው በመካከላቸው ፡ ቆሞ ፡ ሰላም ፡ ለእናንተ ፡ ሲላቸው በእጆቻቸው ፡ ዳስሰዋል ፡ የችንካሩን ፡ ምልክት በእርግጥም ፡ ያ ፡ ኢየሱስ ፡ የተነሳው ፡ ነው ፡ ከሞት ፡ ተነሳ ፡ እንደ ፡ ሌኡቹ ፡ ተነሳ ፡ አልቀረም ፡ በምድር ተነሳ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ፡ ወጥቷል ፡ በክብር ተነሳ ፡ ይመርመር ፡ ይታይ ፡ ተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ይጠና ተነሳ ፡ እንደ ፡ ጌታችን ፡ ተነሳ ፡ ሌላ ፡ የለምና ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ቢጠብቁ ፡ ቢያስጠብቁ ፡ መቃብሩ ፡ ላይ ፡ አትመው ፡ ኦ እነሳለሁ ፡ ብሎ ፡ እንዳለ ፡ እንዳይነሳ ፡ እናድርግ ፡ ብለው ፡ ኦ እንኳን ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ቀርቶ ፡ አልቻለችውም ፡ ምድሪቱ ፡ ኦ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ አሸንፏል ፡ በቃ ፡ ይኸው ፡ ነው ፡ እውነቱ ፡ ኦ

