Gubae

ማደሪያው

Maderiyaw

አዜብ ኃይሉ · ሕያው አምላክ ነህ · 2024

በልቤ ፡ አድሮ ፡ የነበረ ፡ ኮተታ ፡ ኮተት ፡ ቆሻሻው ተጠርጐ ፡ ወጣ ፡ ለቀቀ ፡ ስፍራውን ፡ ለሚገባው ታጠበ ፡ ጸዳ ፡ አማረ ፡ ተሸላለመ ፡ ለጌታ ንጉሤን ፡ ሾምኩት ፡ በልቤ ፡ ሳመልከው ፡ በደስታ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ ውዴ ፡ በበር ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ሲያንኳኳ ፡ ደጄን ፡ ሲመታ የሕይወት ፡ እንጀራን ፡ ይዞ ፡ አዘጋጅሮልኝ ፡ ገበታ ነፍሴን ፡ ሊያጠግባት ፡ ከፍቅሩ ፡ ዘልቆ ፡ ሲገባ ፡ ከቤቴ ነገር ፡ ሁሉ ፡ እንዳልነበረ ፡ ተቀያየረ ፡ ሕይወቴ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ ቃሉን ፡ ገለጠ ፡ ለነፍሴ ፡ የጌታ ፡ መንፈስ ፡ መምህሩ ገብቶኛል ፡ ተረድቻለሁ ፡ ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ነገሩ ውዴ ፡ ሆኖኛል ፡ ለእኔ ፡ እኔም ፡ ለእርሱ ፡ ሆኛለሁ ለሌላው ፡ እንዳልሆን ፡ ሆኜ ፡ በቃል ፡ ኪዳን ፡ ታስሬያለሁ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ ለክብሩ ፡ ለየኝ

አዜብ ኃይሉ · ሁሉም ዘማሪዎች