Gubae

የኔ ናርዶስ

Yene Nardos

አውታሩ ከበደ · እረፍት · 2024

ልትጎበኘኝ ስትመጣ : በቤቴ ስትገባ በቤቴ ለቆኝ ሄደ ያ ብቸኝነቴ :ያ ብቸኝነቴ በቃ አልሄድም መኖሪያዬ : በዚህ ሆኖል ስትለኝ የዘመመው ሊወድቅ ያለው : ቤቴ ጸንቶ ቆመልኝ አንት የኔ ናርዶስ የማትጥለኝ ደግመህ ቤቴ መጣህ ልትጎበኘኝ ምንድ ነው የቀለለኝ ምንድነው ውስጤ ያለው እፎይታ ጠረንህ ይታወቀኛል ጌትዬ መተህ ነው ለካ አንት የኔ ናርዶስ የማትጥለኝ ደግመህ ቤቴ መጣህ ልትጎበኘኝ 3x ብዙ በደል የተተወላት ሴት: ከእግርህ ስር ተደፍታ አለመከች በፈሪሳዊው ቤት ሳይዛት ይሉኝታ የሷ ናርዶስ የሕይወቷ ጠረን የለወጥክላት አንተ እኮ ነህ ሰው በገፋት ግዜ አባት የሆንካት በጇ ያለው ናርዶስ ጠረኑ ጊዜያዊ የርሷ ሽታዋ አንተ ለዘላለማዊ በመንገድ ዳር በወንበዴው በትር ቆስሎ ለወደቀው ሁሉም ሲያልፈው አንስቶ ያከመው ደጉ ሳምርዊ ነው እኔም አለኝ ታሪክ ተመሳሳይ : አንተ ያረክልኝን በምሕረህ ደጉ ሳምራዊ ነህ አንስተህ ያከምከኝ እሱ የከፈለው ካለው ገንዘኑ ነው አንተ የሰጠኸኝ ሕይወትህን ነው

አውታሩ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች