እጆቼን ላንሳ
Ejochien Lansa
አውታሩ ከበደ · ይቅርታ · 2010
ዘማሪ አውታሩ ከበደ ርዕስ እጆቼን ላንሳ አልበም ይቅርታ እጄን አነሳሁ ላመልክህ (፪x) ለፍቅርህ /ለፀጋህ/ የለውም ልክ (፪x) ወዳጅ ነህ (፪x) ወዳጅ ነህ ሲሉህ ቤተኛ ሆንካቸው ልትኖር አብረህ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉህ መላዕክቱ በዜማ (፪x) የአንተን ታላቅነት ቀርቦ ላየህማ (፪x) ውጡ ውጡ አይልም በዛው ቅሩ እንጂ (፪x) የፍቅርህ ጠረን አያስመኝም ውጪ (፪x) የምህረትህ ብዛት የፍቅርህ ዳር በሰላም ጠበቀኝ እንዳልሸበር የተነሳው ወጀብ ታንኳዬን ሊሰብረው ሳይነካኝ አለፈ ስላለኝ ቅጥር (፪x) እጄን አነሳሁ ላመልክህ (፪x) ለፍቅርህ/ለፀጋህ/ የለውም ልክ (፪x) ቅዱስ ቅዱስ ሲሉህ መላዕክቱ በዜማ (፪x) የአንተን ታላቅነት ቀርቦ pላየህማ (፪x) ውጡ ውጡ አይልም በዛው ቅሩ እንጂ (፪x) የፍቅርህ ጠረን አያስመኝም ውጪ (፪x)

