Gubae

ደግሞ ቀኑ ሲጨልም

Degmo Qenu Sichelm

አውታሩ ከበደ · ተነስቷል · 2007

ጠዋት ፡ ስነሳ ፡ ደስታ ፡ ይሆናል የትላንትናው ፡ ሃዘን ፡ ይርቃል እህል ፡ ባልበላም ፡ ፊትህ ፡ ያጠግበኛል ፀጋህ ፡ ከክፉ ፡ ይጋርደኛል ምህረትህ ፡ ከፊት ፡ ከኋላ ፡ ከቦኝ አቤት ፡ ይገርማል ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩት አዝ፦ ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲነጋ ደግሞ ፡ እርጥቡ ፡ ሲደርቅ ደግሞ ፡ ሁኔታ ፡ ሲርቅ አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል አምላክ ፡ ሲረዳኝ ፡ አታዩም ፡ ዎይ ክረምቱ ፡ አልፎ ፡ በጋው ፡ ሲታይ ከዓለቱ ፡ ልውጣ ፡ ድምጼን ፡ ላሰማ ጌታ ፡ እንደ ፡ ረዳኝ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይስማ ያገለገልኩት ፡ ለሥሙ ፡ የለየኝ ቀን ፡ ቆጠረና ፡ ዋጋ ፡ ከፈለኝ አዝ፦ ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨልም ደግሞ ፡ ቀኑ ፡ ሲነጋ ደግሞ ፡ እርጥቡ ፡ ሲደርቅ ደግሞ ፡ ሁኔታ ፡ ሲርቅ አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል አንዴ ፡ ወዶኛል (፬x) ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል

አውታሩ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች