ይልፈኝ
Yilefegn
አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024
ይለፈኝ ባለማዕረጉ ይለፈኝ ባለጸጋው ይለፈኝ አጃቢ ያለው ይለፈኝ ባለጊዜው ይለፈኝ ያልኩት ወዳጄ ይለፈኝ የበላ ከእጄ ይለፈኝ ዘመዴ ያልኩት ገበናዬን ገልጬ ያሳየሁት አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህቺ ቀን ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን በፍቅርህ የተገፉትን የምታቀርብ በትከሻህ የዛሉትን የምትሸከም በክንፎችህ ታናናሾችን ትይዛለህ በርህራሄ አይኖችህ የተጣለውን ታነሳዋለህ በፍቅርህ የተገፉትን የምታቀርብ በትከሻህ የዛሉትን የምትሸከም በክንፎችህ ታናናሾችን ትይዛለህ በርህራሄ አይኖችህ የተጣለውን ታነሳዋለህ ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለጠናበት ቃልህ ሰላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት በብር እና በወርቅ ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ በበዛው ሰላምህ እየተትረፈረፈ ጣትህ ፈውስ ነው ህመም ለጠናበት ቃልህ ሰላም አለው ሃዘን ለገባው ቤት በስጦታህ ብዛት ሳይሆን አንተን ሰምቶ ስንቱ አረፈ በበዛው ሰላምህ እየተትረፈረፈ ይለፈኝ ሰው የጓጓለት ይለፈኝ የሚሯሯጥለት ይለፈኝ ከፍ ብሎ የታየው ይለፈኝ ለስጋ የሆነው ይለፈኝ የሚመስል ከፍታ የተናቀ በአንተ እይታ ነገር ግን ከአንተ ለሆነው ይኸው እጄን ከፍ አድርጌአለሁ አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህች ቀን ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን ለቁስል የሚሆን ዘይት በእጅህ አለ ያልጀመረ በኔ ስንቱን ቤት ያከመ ዛሬም ከኔ ደርሶ አይቀንስ ጉልበቱ ፈሶ ያድነኛል ያደርገኛል ብርቱ ለአንተ ብቻ እንድሆን ካዛለኝ ሸሽቼ ሃሳቤን መንገዴን ሁሉዬን ሰጥቼ በደነገለ ህይወት በማይሆን ለሌላ ሆኜ ልለቅልህ ፈጥነህ አግኘኝና አትለፈኝ በቃልህ አትለፈኝ ኢየሱሴ አትለፈኝ ሳትነካኝ አትለፈኝ መጽናኛዬ መንፈስህ ሳይነካኝ አትለፈኝ ይህች ቀን ፈቃድህ ሳይፈጸም አትለፈኝ ይህች ቀን ቃልህ ሳይበራልኝ አትለፈኝ ይህች ቀን የልብህን ሳትነግረኝ አትለፈኝ ይህች ቀን

