ወደ ተራራው ጫፍ
Wede Teraraw Chaf
አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024
ከህልውናህ ፡ ሰፈር ፡ ከምትገኝበት ንግግር ፡ ፀሎቴ ፡ አንተው ፡ ከሆንክበት ጠንቀቅ ፡ ካላልኩኝ ፡ ካልጠበቅሁ ፡ እግሮቼን እልፍ ፡ የሚለይ ፡ ጉዳይ ፡ ከቦኛል ፡ ዙሪያዬን በገለባ ፡ ናፍቆት ፡ በጠፊ ፡ ፍለጋ አይለፍብኝ ፡ ቀኔ ፡ አርቆኝ ፡ ካንተ ፡ ጋር ወደተራራው ፡ ጫፍ ፡ ሳበኝ ፡ ወደራስህ ነፍሴም ፡ ድና ፡ እንድትቀር ፡ አቅልጣት ፡ በክብርህ (፪x) መባዘን ፡ አይደለም ፡ መዋል ፡ ካንተ ፡ ጋራ ስለ ፡ ላዩ ፡ ምክርህ ፡ ነፍሴን ፡ ስታዋራ ሰብሰብ ፡ ብሏል ፡ ቀኔ ፡ አልተዝረከረከም የማይወሰድ ፡ እድል ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ የለም አንተን ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ የማይበት ፡ ዓይኔ ልቤም ፡ ሄዶ ፡ ይቅር ፡ ከላዩ ፡ ሰፈሬ ጆሮዬም ፡ ይቀስር ፡ ከላይኛው ፡ ሃገር አጥፋኝ ፡ ከምድሩ ፡ ፍለጋዬ ፡ ይሰወር አንገቴን ፡ አስግጌ ፡ በመናፈቅ ፡ ህይወት ለአፍታ ፡ ጎንበስ ፡ ሳልል ፡ አንዳች ፡ ከሌለበት እጅ ፡ ሰጥቶ ፡ ላንተ ፡ ውስጥና ፡ ውጪዬ ስንቄ ፡ ሆኖ ፡ ፍቅርህ ፡ ይጠቅለል ፡ እድሜዬ (፪x) ጥሜ ፡ ረሃቤ ፡ ናፍቆቴ ፡ መሻቴ ጉጉቴ ፡ ፍላጎቴ ፡ ሩጫዬ ፡ መገስገሴ አንተን ፡ ለማግኘት ፡ ነው (፪x) በቃ ፡ ፈልግሃለሁ ፡ በቃ ፡ ተርቤሃለሁ በቃ ፡ በጣም ፡ ጠምተኸኛል ፡ በቃ ፡ አይኖቼ ፡ ናፍቀውሃል በቃ ፡ ናፍቄሃለሁ ፡ በቃ ፡ ደጅ ፡ ደጅ ፡ አያለሁ በቃ ፡ የውስጤ ፡ ጥም ፡ ነህ በምንም ፡ የማልለውጥህ አንተን ፡ የተራበ ፡ ሚጠግበው ፡ አንተን ፡ ነው አንተን ፡ የተጠማ ፡ ሚረካው ፡ አንተን ፡ ነው ፊትህን ፡ የፈለገ ፡ ሲያገኝህ ፡ ያርፋል ፈልጎ ፡ ክብርህን ፡ መቼ ፡ በጅህ ፡ ይረካል አይደለሁም ፡ ሰነፍ ፡ ተመከርኩ ፡ በቃልህ የውስጤን ፡ እረሃብ ፡ አይደፍነውም ፡ የእጅህ ነፍሴን ፡ የምታረካ ፡ ሙላት ፡ ነህ ፡ የልቤ የኑሮዬ ፡ ፍሰሃ ፡ የዕድሜ ፡ ልክ ፡ ሃሳቤ

