ሃሌሉያ
Hallelujah
አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024
በሰላሙ ፡ ብዛት ፡ ቀለለ ፡ ችግሩ አደገ ፡ ቁመቴ ፡ እያለ ፡ ነገሩ ቀረ ፡ መዋከቤ ፡ በጠራኸኝ ፡ ሳርፍ ተምራልኝ ፡ ነፍሴ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ማራገፍ ድምጿ ፡ ተቀየረ ፡ ተለወጠ ፡ ቃ እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን ለለወጥከው እየሱስ እንካ ዘላለሜን እዬዬን ፡ በእሰየው ፡ የአንተ ፡ በመሆኗ እህህን ፡ በእልልታ ፡ ለምኑን ፡ በአሜን ለቀየርከው ፡ እየሱስ ፡ እንካ ፡ ዘላለሜን ተባረክ ፡ እልሃለሁኝ (፰x) ተንበርክኬ ፡ አሸነፍኩኝ እጅ ፡ ሰጥቼ ፡ ድል ፡ ነሳሁኝ በጩኸቴ ፡ መዳን ፡ ሆነ አበሳዬ ፡ ተከደነ ተከትዬህ ፡ ከፊት ፡ ቀደምኩ ያንተን ፡ ብዬ ፡ ከምን ፡ ጎደልኩ ስፈልግህ ፡ ጸኑ ፡ እግሮቼ ፡ ሃይሌ ፡ ሆነኸኝ ፡ ተሟጋቼ በመጨነቅ ፡ ስርአትህን በመማጸን ፡ መጓደድን በር ፡ በመዝጋት ፡ ክፉን ፡ ማምለጥ እርዳኝ ፡ ብዬ ፡ ሁሉን ፡ መብለጥ ከአንተ ፡ ሰምቶ ፡ የውስጥ ፡ ውበት አቤት ፡ ብዬህ ፡ አለኝ ፡ ማለት ከአንተ ፡ ዘግኖ ፡ ሞልቶ ፡ ማደር ሆኖልኛል ፡ ስምህ ፡ ይክበር ስኬቴ ፡ በአንተ ፡ መታመኔ ከፍታዬ ፡ እግርህ ፡ ስር ፡ መሆኔ ውበቴ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ ድምቀቴ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለኔ ስኬቴ ፡ በአንተ ፡ መታመኔ ከፍታዬ ፡ እግርህ ፡ ስር ፡ መሆኔ ውበቴ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ ድምቀቴ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለኔ አሃ ሃሌሉያ/4 እላለሁ ሃሌሉያ በማለዳ ሃሌሉያ በቀትር ሃሌሉያ በምሽት ፡ ሃሌሉያ ፡ በሌሊት ፡ ሃሌሉያ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ ፡ ሃሌሉያ ሳይቀየር ፡ ሃሌሉያ እላለሁ ፡ ሃሌሉያ አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፪x) ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ አሃ ፡ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ሃሌሉያ

