ጉዳዬ
Gudaye
አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024
ለሚያወራህ ፡ ውበት ፡ ለሚለብስህ ፡ ጌጥ ሮጦ ፡ ለተጠጋህ ፡ የማምለጫ ፡ አለት ህይወት ፡ ከሞት ፡ ወዲያ ፡ እርስቱ ፡ ላረገህ ለአፍታ ፡ እንኩዋን ፡ የማትጎድል ፡ ለሰው ፡ ሙላቱ ፡ ነህ አንተን ፡ ነው ፡ እንጂ ጥብቅ ፡ አድርጎ ፡ መያዝ ፡ ያዘኝ ፡ እያሉ ማልዶ ፡ በጠዋት በአንተው ፡ እጅ ፡ ነቅቶ ፡ መዋል ፡ ደጅ ፡ እየጠኑ (፪x) ዓይኔን ፡ ጉዳዬ ፡ ላይ ፡ ማድረግ ፍለጋዬን ፡ እድሜ ፡ ልክ ፡ መፈለግ ናፍቆቴን ፡ ሳላርፍ ፡ መናፈቅ ጉጉቴን ፡ ሳልደክም ፡ መፈለግ እንዲሆንልኝ ፡ ይብዛልኝ ፡ ጸጋህ ጊዜው ፡ ደርሶ ፡ እስክደርስ ፡ አንተ ፡ ጋር ገባ ፡ ወጣ ፡ እግሬ ፡ ሳይልብኝ ፡ ፍለጋዬ ፡ ሳትጎድል ፡ ብዛልኝ በድነቴ ፡ ጠዋት ፡ በገባኸኝ ፡ ማግስት ጨዋታ ፡ ወሬዬ ፡ መወደዴን ፡ ማድነቅ ዘምሬህ ፡ አልጠግብ ፡ አውርቼህ ፡ አልረካ ይህቺ ፡ ትንሽ ፡ ልቤ ፡ ለፍቅርህ ፡ ሸፍታ አልደግ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ እራሴን ፡ አልቻል አጓጉል ፡ ነው ፡ ሁሉም ፡ ያላንተ ፡ መች ፡ ያምራል መጠበቂያ ፡ አጥሬ ፡ መሰንበቻዬ ፡ ነህ ልኑር ፡ እንደፈዘዝሁ ፡ ዓይኔ ፡ አንተን ፡ እያለ ጉዳዬ ፡ አንተው ፡ መናፈቄ ፡ መምጣትህ ጉጉቴ ፡ ዓይኔ ፡ እስከሚያይህ ሁሌ ፡ ሁሌ ፡ ሁሌ ፡ ሁሌ ፡ አንተን ፡ ብቻ እስከ ፡ እድሜዬ ፡ መቋጫ (፬x) ዓይኔን ፡ ጉዳዬ ፡ ላይ ፡ ማድረግ ፍለጋዬን ፡ እድሜ ፡ ልክ ፡ መፈለግ ናፍቆቴን ፡ ሳላርፍ ፡ መናፈቅ ጉጉቴን ፡ ሳልደክም ፡ መፈለግ እንዲሆንልኝ ፡ ይብዛልኝ ፡ ጸጋህ ጊዜው ፡ ደርሶ ፡ እስክደርስ ፡ አንተ ፡ ጋ ገባ ፡ ወጣ ፡ እግሬ ፡ ሳይልብኝ ፡ ፍለጋዬ ፡ ሳትጎድል ፡ ብዛልኝ

