Gubae

ፍለጋው አደረገኝ

Filegaw Aderegegn

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

እንደገናን ፡ ባያውቅ ፡ ዳግም ፡ ዕድል ፡ ባይሰጥ ማን ፡ ይችል ፡ ነበረ ፡ የጌታን ፡ ደጅ ፡ ሊረግጥ እየተደገፈ ፡ በማይሰፈር ፡ ፀጋው እንደኔ ፡ የቆመ ፡ ስንቱን ፡ ቤት ፡ ይቁጠረው ስንቱን ፡ ቤት ፡ ይቁጠረው (፪x) ደጋግሞ ፡ የተፈተነ ፡ እምነቴ እንዳይንኮታኮት ፡ አልቆለት ፡ እንዳይወድቅ እንደስንዴ ፡ ሊያበጥረኝ ፡ የወጣውን ፡ ፈታኝ በ ፡ ‘አይቻልም’ ፡ ሲሰድ የአንደበቴን ፡ ሳይሆን ፡ ያወቀ ፡ የልቤን እንደተመኘሁት ፡ ልሆን ፡ ያለመቻሌን እስኪቆሙ ፡ እግሮቼ ፡ በብዙ ፡ አገዘኝ ሃይልን ፡ እስክቀበል ፡ አይዞሽ ፡ በርቺ ፡ እያለኝ ያለቀልኝ ፡ መስሎት ፡ ለሳቀብኝ ፡ ጠላቱ ማልዶ ፡ ማለደልኝ ፡ ጉልበቴን ፡ አጸናት (፪x) ክህደት ፡ መሃላዬን ፡ አላውቀውም ፡ ማለቴን ዶሮ ፡ ሶስቴ ፡ እስኪጮህ ፡ አልፎ ፡ መጨመሬን ከትንሳኤው ፡ ማግስት ፡ ብርቱዎች ፡ እያሉ ከሰነፎች ፡ ተርታ ፡ እንደኔ ፡ ያልዋሉ ፍልጋው ፡ አረገኝ ፡ መጣ ፡ ወዳለሁበት ሊቀጥለኝ ፡ ዳግም ፡ ከተቆረጥኩበት ፍለጋው ፡ አደረገኝ ፡ መጣ ፡ ወዳለሁበት (፬x) በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው በማለዳ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው ለተቤዠኝ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው በማይጠቅሙት ፡ መጠቀም ፡ ልማዱ ፡ ለሆነው ሳላቋርጥ ፡ ምስጋናዬ ፡ ይኸው በትንሽ ፡ አዕምሮዬ ፡ ስላሰብኩት ፡ ነገር ብዕሬን ፡ ይዣለው ፡ ቃላትን ፡ ቀምሬ ፡ በዜማ ፡ ልናገር አልችልም ፡ ልደብቅ ፡ የውስጥ ፡ ደስታዬን እሱ ፡ በኔ ፡ ሆኖ ፡ ነውሬን ፡ አስወግዶ ፡ ከሰው ፡ መቆጠሬን ዝም ፡ ይባላል ፡ እንዴ ፡ ደግሞስ ፡ ያስችላል ፡ ወይ አትረፍርፎ ፡ አድርጎልኝ ፡ ረድኤቱን ፡ ከላይ የቃላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ያለፈ ፡ መውደድ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ የራሱ ፡ የሚያደርግ አጽናንቶኛል ፡ ባድማ ፡ ህይወቴን ፡ በመልካምነቱ ፡ ሞልቶ አስደሰተኝ ፡ በረሃ ፡ ህይወቴን ፡ እንደ ፡ ኤደን ፡ አድርጎ ተድላ ፡ አደለኝ ፡ የደስታ ፡ የቅኔ ፡ ድምጽ ፡ ወጣ ፡ ከቤቴ መራቄ ፡ ቀርቶ ፡ ቀርቤአለሁ ፡ አብ ፡ ሆኖኝ ፡ አባቴ (፪x) በትንሽ ፡ አዕምሮዬ ፡ ስላሰብኩት ፡ ነገር ብዕሬን ፡ ይዣለው ፡ ቃላትን ፡ ቀምሬ ፡ በዜማ ፡ ልናገር አልችልም ፡ ልደብቅ ፡ የውስጥ ፡ ደስታዬን እሱ ፡ በኔ ፡ ሆኖ ፡ ነውሬን ፡ አስወግዶ ፡ ከሰው ፡ መቆጠሬን ዝም ፡ ይባላል ፡ እንዴ ፡ ደግሞስ ፡ ያስችላል ፡ ወይ አትረፍርፎ ፡ አድርጎልኝ ፡ ረድኤቱን ፡ ከላይ የቃላትን ፡ ድንበር ፡ ጥሶ ፡ ያለፈ ፡ መውደድ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ የራሱ ፡ የሚያደርግ

አስቴር አበበ · ሁሉም ዘማሪዎች