Gubae

ፈልጌህ

Felegieh

አስቴር አበበ · ክብር የበቃህ ነህ · 2017

ፈልጌህ ፡ አላጣሁህም ከልቤ ፡ ሽቼህ ፡ ራስህን ፡ አልሰወርክም (፪x) ውሃ ፡ በሌለበት ፡ በደረቅ ፡ ምድር ነፍሴ ፡ ተጠምታ ፡ አገኘችህ ፡ አገኘችህ (አገኘችህ) ፪x በቅቤና ፡ በስብ ፡ እንደሚረካ ፡ ሰው ሳገኝህ ፡ ልቤን ፡ ደስ ፡ አለው (፪x) ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አባትነትህ ዘላለም ፡ በቤቴ ፡ እራስ ፡ ሁን ፡ የምልህ ተመችቶኝ ፡ ነው ፡ አምላክነትህ ዘላለም ፡ በላዬ ፡ ንገስብኝ ፡ ምልህ አዛኝ ፡ ባትሆን ፡ ፍቅር ፡ ባትሆን ፡ አምላኬ ፡ ባትሆን ፡ ጌታዬ ፡ ባትሆን ባትሸከመኝ ፡ በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ መክረህ ፡ ባትመልሰኝ በፍቅር ፡ ባትይዘኝ ፡ ፈቅደህ ፡ ባትምረኝ ፡ ምክርህ ፡ ባይደግፈኝ ምን ፡ ይሆን ፡ ነበረ ፡ ዕጣዬ ስለምሕረትህ ፡ ተመስገን ፡ ጌታዬ (2x) አቅም ፡ የሆንክልኝ ፡ ተባረክ ዘውዴ ፡ መድመቂያዬ ፡ ተባረክ ቅድስናዬ ፡ ነህ ፡ ተባረክ አብ ፡ ፊት ፡ መታያዬ ፡ ተባረክ (፪x) ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ ተባረክ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ተባረክ እኔ ፡ ምፈልገው ፡ (አንተን ፡ ነው) (፫x) ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x) ሁሌ ፡ ምናፍቀው (አንተን ፡ ነው) (፫x) ሌላው ፡ በሙሉ (ቀሪ ፡ ነው) (፫x) እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው ሌላው ፡ በሙሉ ፡ ቀሪ ፡ ነው እኔ ፡ ምፈልገው ፡ አንተን ፡ ነው ሌላው ፡ በሙሉ ፡ (ቀሪ ፡ ነው) (፮x)

አስቴር አበበ · ሁሉም ዘማሪዎች