Gubae

ብዛልኝ

Bizalign

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ቦታ ፡ ለምኔ ሃገር ፡ ለምኔ ፡ ከፍታ ፡ ለምኔ አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ህብረት ፡ ለምኔ መዝሙር ፡ ለምኔ ፡ ወሬ ፡ ለምኔ (፪x) አስጠጋኝ ፡ ወደ ፡ እቅድህ ወዳየህልኝ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ (፪x) የእግሮቼን ፡ ጉዞ ፡ መትርልኝ የአንደበቴን ፡ ቃል ፡ ስፈርልኝ ለፈቃዴ ፡ ገደብን ፡ አብጅለት ሞገደኛው ፡ ልቤ ፡ ይወቅ ፡ ለከት አስተምረኝ ፡ ምን ፡ ትላለህ ፡ ማለት (፪x) አይኖቼ ፡ እያዩ ፡ ቅጥቅጧን ፡ ሸንበቆ ፡ ደግፈህ ፡ ስታቆመኝ እያወቀ ፡ ልቤ ፡ የምጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ቀርበህ ፡ ስታበራኝ ጆሮዬ ፡ እየሰማ ፡ ለራስ ፡ ማልበቃውን ፡ ስታተርፈኝ ፡ ለሃገር በቀረልኝ ፡ እድሜ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ውጪ ፡ አፌ ፡ ምን ፡ የናገር አሁንም ፡ ብዛልኝ ፡ እንዲረዝም ፡ እድሜዬ አብልጬ ፡ ልጠጋህ ፡ እንዲደምቅ ፡ ማታዬ ሁነኝ ፡ መዋያዬ ፡ በቀረልኝ ፡ ዘመን መንገዴ ፡ እየነጋ ፡ እስኪሆን ፡ ሙሉ ፡ ቀን (፪x) ዉሎ ፡ ካንተ ፡ ጋር ፡ አድሮና ፡ ሰንብቶ ማን ፡ በትናንት ፡ ቀረ ፡ ከአንተ ፡ ብዙ ፡ ቀድቶ የለውጥ ፡ ጅማሬ ፡ ነህ ፡ የሕይወት ፡ ማጣፈጫ የተጠጉህ ፡ ሁሉ ፡ ወጥተዋል ፡ በብልጫ (፪x) ሰሞነኛ ፡ እንዳልሆን ፡ አድሮ ፡ እንዳልሰለች ጉልበቴን ፡ ላስጠጋ ፡ ወደ ፡ ቃሎችህ ፡ ደጅ ዘመንን ፡ ዘላቂ ፡ እንዲሆን ፡ ነገሬ ዙረቴን ፡ አቁሜ ፡ ልፈልግህ ፡ ዛሬ

አስቴር አበበ · ሁሉም ዘማሪዎች