በቃኝ የማልለው
Bekagn Yemalilew
አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024
እንደገና ፡ ረሃብ ፡ እንደገና ፡ ጥማት ትናንት ፡ ምንም ፡ እንዳላየ እንደገና ፡ ናፍቆት ፡ እንደገና ፡ ጉጉት አንተ ፡ ወዳለህበት (፪x) ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው ዕለት ፡ ዕለት ፡ ባዶ ፡ ትሁንና ፡ ነፍሴ በመገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ ይረስርስ ፡ መንፈሴ (፪x) በቃኝ ፡ የማልለው ፡ ይለፈኝ ፡ የማልለው ሰለቸኝ ፡ የማልለው ፡ ያንተ ፡ ሕልውናህ ደስታዬ ፡ ያለበት ፡ ያለፈ ፡ ሰላሜ መገኘትህ ፡ ነው ፡ መዋያ ፡ ማደሪያዬ ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሕልውናህን ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ በላይ ፡ ያለውን ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን የፊትህን ፡ ሳይሆን ፡ ፈልጎ ፡ የእጅህን ባትገባም ፡ ከቤቴ ፡ ላክ ፡ ብቻ ፡ ቃልህን የእምነቱን ፡ ቁመት ፡ አድንቀህ ፡ እንዳለፍከው አንተን ፡ በደጅ ፡ ትቶ ፡ ፈውሱን ፡ ብቻ ፡ እንዳለው አይደል ፡ መገስገሴ ፡ ፊትህን ፡ ማለቴ ማድጋዬን ፡ ልሞላ ፡ ላሰማምር ፡ ቤቴን ይህን ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ክነዝብርቅርቁ ካንተ ፡ ካልከተመኝ ፡ ካቆመኝ ፡ በሩቁ ሳበኝ ፡ በእጆችህ ፡ ወደ ፡ ክብርህ ፡ ጥልቅ አስገባኝ ፡ ከእልፍኝህ ፡ ጅምሩም ፡ ባያልቅ በቃኝ ፡ የማልለው ፡ ይለፈኝ ፡ የማልለው ሰለቸኝ ፡ የማልለው ፡ ያንተ ፡ ሕልውናህ ደስታዬ ፡ ያለበት ፡ ያለፈ ፡ ሰላሜ መገኘትህ ፡ ነው ፡ መዋያ ፡ ማደሪያዬ (፪x)

