Gubae

አሜን

Amen

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

ውሉን አልሳተም የህይወቴ ድውር ስትክሰኝ አየሁ ስታሰማምር አንድ ብለህ እንደ ጀመርክ ብክብር ስለምትቋጨው ዝም ብዬ ልዘምር ይሁን አንተ እንዳልከው ያልከው ይሁን እሺ እሺ በቃ ነፍስ ትረፍልኝ ያልክላትን አውቃ በወደድኩት ሳይፈስ ለኔ በተመቸኝ የህይወቴ ጎዳናው ለምን ሲያሰኘኝ ሁሉን አያይዞ ለበጎ ሲያደርግ በዓይኔ በብረቱ አየሁት ሲለውጥ ርስቱን ሲያድል ነጥቆ ከዚያ ሰነፍ ዘወትር ለሚተጋው ሊያልቀው ሲሰለፍ ትናንት እንደሆነው ዛሬም እንደዚያው ነው ስፍራን ላልለቀቀ በቦታው ለቆየው አሜን አሜን ያለው ይሁን እሺ እሺ በቃ ነፍስ ትረፍልኝ ያለላትን አውቃ የገዢ ቁጣ ሲነድ በላዬ ፍንክች ላልል ላለቅ ስፍራዬን በትዕግስት ስፋት መቆየት ላደርግ ታላቁን ጥፋት ፀጥ እስክታደርግ እንድኖር በቃልህ ልቤን አስፋልኝ ቀን እስኪመጣ እስክትፈርድልኝ ያደከመኝን እክታደክመው የበቀል ጣትህን ዓይኔ እስኪያየው ድቅድቁን ስታዝዝ ላይቀር መንጋቱ ጎህ ሊቀድልኝ ሊያልፍ ሌሊቱ የቀረ ይመስላል አንዲት እርምጃ ተራራው ሊናድ ሊሆን መሄጃ የወጀቡ አዛዥ የተራራው ሠሪ የሸለቆው ጌታ የጨለማው መሪ የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ አንተ ነህ የኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ የወጅቡ አዛዥ የተራራው ሠሪ የሸለቆው ጌታ የጨለማው መሪ የማዕበሉ አዝማች የመብረቁ ንጉስ አንተ ነህ የኔ አባት የእስራኤል ቅዱስ

አስቴር አበበ · ሁሉም ዘማሪዎች