Gubae

አመልክሃለው

Amelkihalehu

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

እረሳሁት ፡ ጥያቄዬን የከበበኝን ፡ በዙሪያዬ ስቀርብ ፡ ፊትህ ፡ ለማመስገን ቀሎ ፡ ታየኝ ፡ ሁሉም ፡ ነገር (፪x) ሳላመልክህ ፡ ጊዜው ፡ አይለፍ የሚገባህን ፡ ምስጋና ፡ ሳላቀርብ ሞልቶ ፡ ላይሞላ ፡ የምድሩ ፡ ነገር ካልክልኝ ፡ አልጎድልም ፡ ለጭንቅ ፡ ውሎ ፡ ማደር ርቋል ፡ ከኔ ፡ ሰፈር (፪x) አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ ለተራራው ፡ ቁመት ፡ እያልኩኝ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ለሸለቆው ፡ ጥልቀት ፡ እያልኩኝ ፡ ሙላት ፡ ነህ ለሞገዱ ፡ ብርታት ፡ እያልኩኝ ፡ ሰላም ፡ ነህ ለጨለማው ፡ ርዝመት ፡ እያልኩኝ ፡ ብርሃን ፡ ነህ አመልክሃለው (፫x) ፡ በማደሪያዎችህ ፡ መካከል ፡ ቆሜ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ታገልኩ ፡ ከቃላቶች ፡ ጋራ ስላንተ ፡ ማንነት ፡ በዝርዝር ፡ ላወራ አንሰው ፡ ተገኙብኝ ፡ ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ አላረካኝ እንደገባኝ ፡ መጠን ፡ እንኳን ፡ ልገልጽህ ፡ አቃተኝ (፪x) ማንም ፡ እንደሚልህ ፡ አይደለህም ከመታወቅ ፡ ታልፋለህ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x) ትልቅ ፡ ነህ (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፬x) ካነበብኩት ፡ አይደል ፡ ከሰው ፡ የሰማሁት ዛሬ ፡ በዚህ ፡ ሰዓት ፡ ፊትህ ፡ ያመጣሁት ከነፍሴ ፡ ምስጋና ፡ ከውስጠቷ ፡ የሆነ አፌን ፡ ሞልቶ ፡ የሚፈስ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ አለ (፪x) ያላነሰ ፡ ያላጠረ ከላይ ፡ ከላይ ፡ ያልሆነ ለእኔ ፡ ፍቅር ፡ ለኢየሱሴ አለኝ ፡ ምስጋና ፡ ከነፍሴ (፪x)

አስቴር አበበ · ሁሉም ዘማሪዎች