ክብሬ
Kebrie
አስማማው ቢረሳው · የመኖር ምክንያቴ · 2012
{ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X) ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ {አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X) አስመልጦኛል ፡ ታሪክን ፡ ሠርቶ በቀራንዮ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፍሎ ታዲያ ፡ ለኢየሱስ ፡ ለሆነኝ ፡ ሕይወት መች ፡ ይበቃዋል ፡ ብዘምርለት? {ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X) ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ {አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X) ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ክብር ለአንተ ፡ ብቻ ፡ አምልኮ ይገባሃል ፡ ስግደት ይገባሃል ፡ አምልኮ ለዘለዓለም ፡ ክበር ክበር ፡ ለዘለዓለም ። ሸክሜ ፡ ከላዬ ፣ ተንከባለለ ይኸው ፡ ዛሬማ ፣ ቀና ፡ ብያለሁ ተቀይሮልኝ ፡ ሁሉ ፡ ታሪኬ ዕጣ ፡ ደረሰኝ ፡ ሆንከኝ ፡ አምላኬ ። {ክብሬ ፣ ልበልህ ፡ ክብሬ ወጌ ፣ ልበልህ ፡ ማዕረጌ በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ማለፌ} (፪X) ከዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ስበህ ፡ ላወጣኸኝ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ላደረግህልኝ {አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ አለኝ ፡ ክብር ፡ አለኝ አለኝ ፡ ውዳሴ ፡ አለኝ አለኝ ፡ ቅዳሤ ፡ አለኝ} (፪X)

