Gubae

አንተ የእኔ

Ante Yenie

አስማማው ቢረሳው · የመኖር ምክንያቴ · 2012

አሃ! አሃሃ! (፪x) በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አስፍሮኛል አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል (፪x) አዝ፦ አዎ! እኔ ፡ የእርሱ አዎ! እርሱም ፡ የእኔ አዎ! የማገኘው አዎ! ሁሌ ፡ ከጐኔ (፪x) አሃ! አሃሃ! (፪x) የከበረ ፡ ዋጋ ፡ ተከፍሎልኝ በደሙ ፡ የተገኘሁ ፡ ልጁ ፡ ነኝ አይደለም ፡ ጠላቴ ፡ እንደሚለው መላው ፡ እኔነቴ ፡ የእርሱ ፡ ነው የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x) ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ ዓላማው ፡ ፍቅር ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለው ከሚያደርገው ፡ ነገር ፡ የማየው እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ፡ የሚጠብቀኝ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ለእኔ ፡ ሊሆንልኝ የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x) ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አስፍሮኛል አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል (፪x) አዝ፦ አዎ! እኔ ፡ የእርሱ አዎ! እርሱም ፡ የእኔ አዎ! የማገኘው አዎ! ሁሌ ፡ ከጐኔ (፪x) አሃ! አሃሃ! (፪x) ውብና ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ የፈጠረኝ ለምሥጋናው ፡ ለአምልኮ ፡ ያጨኝ የተፈጠርኩበት ፡ ውድ ፡ ዓላማ ስለገባኝ ፡ ለእኔ ሌላ ፡ አልሰማም የጌታ ፡ ነኝ ፣ የጌታ ፡ ነኝ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፣ የኢየሱስ ፡ ነኝ ማንም ፡ አይችልም ፣ ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ ፣ ሊነጥለኝ (፫x) ማንም ፡ አይችልም ሊነጥለኝ

አስማማው ቢረሳው · ሁሉም ዘማሪዎች