Gubae

ዛሬም ክበርልኝ

Zarem Kiberlgn

አስፋው መለሰ · በጅምር አይቀርም

እኔ አምልክሃለሁ በደስታ ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2 ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን አስረስተኸኛል መከራዬን/2 ክፉ ያልኳቸውን ቀኖች አሳለፍከኝ በእጆችህ ደግፈህ ዛሬንም አቆምከኝ/2 ምህረት ቸርነትህ እየተከተሉኝ በክንፎችህ ጥላ በቤትህ አለሁኝ/2 እኔ አምልክሃለሁ በደስታ ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2 ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን አስረስተኸኛል መከራዬን/2 ለክፉ የተመኘኝ ሊያጠፋኝ የወጣ አፍሮ ተመለሰ ቃል ካፍህ ሲወጣ/2 ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊቴ ወጣና ከፍታውን ሰጠኝ አስረገጠኝና/2 እኔ አምልክሃለሁ በደስታ ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2 ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን አስረስተኸኛል መከራዬን/2 ዳግም ላይታሰብ የትላንቱ ችግር እልፍ አደረገኝ ወዳየልኝ ክብር/2 በዙሪያዬ ከበው ነፍሴን ግራ ያጋቡ ዛሬ አጣኻቸው ወዴት እንደገቡ/2 እኔ አምልክሃለሁ በደስታ ዛሬም ክብርልኝ የኔ ጌታ/2 ሸክሜን ወሰድከው አበሳዬን አስረስተኸኛል መከራዬን/2

አስፋው መለሰ · ሁሉም ዘማሪዎች