አምላኬ
Amlake
አስፋው መለሰ · በጅምር አይቀርም · 2005
ዘማሪ አስፋው መለሰ አምላኬ ማነው ምሸከመን ሰብስቦ አሳዳጊ የፍቅር ልብ ያለው የጠፋን ፈላጊ አልባሽ አጣን እኮ እርቃንን የሚሸፍን ማነው ለኛ ዛሬ አባት የሚሆን ማነው ምሸከመን ሰብስቦ አሳዳጊ የፍቅር ልብ ያለው የጠፋን ፈላጊ አልባሽ አጣን እኮ እርቃንን የሚሸፍን ማነው ለኛ ዛሬ አባት የሚሆን አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኛ ማን ይሆናል አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኔ ማን ይሆናል የቱ ነው እረኛው መንጋውን ጠባቂ ጠብቆ ሚያሳድግ ከአውሬ ከነጣቂ ሰምቶ የሚያሰማን ስጠን ባለራዕይ አይኖቹ የበሩ አጥርቶ የሚያይ አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኛ ማን ይሆናል አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኔ ማን ይሆናል ነገር ጨላልሞበት ግራ ለተጋባው ምድረበዳው ኑሮ ተስፋ ላሳጣው ሰው አሩሩ በዝቶበት ለሚቅበዘበዘው እግዚአብሄር እንዳንተ የሚያሳርፍ ማነው አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኛ ማን ይሆናል አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን ለኔ ማን ይሆናል

