የመጨረሻዬ
Yemechereshayie
አገኝሁ ይደግ · ሃሌሉያ ታላቅ ነህ · 2004
ዓለም ስትንጫጫ ወከባ ሲበዛ ለእኔ ግን አንተው ነህ የዘለዓለም ቤዛ መሸሸጊያዬ ነህ ይሄው አስከዛሬ አሁንም አደራ አድርሰኝ አገሬ(፪) መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ እየሱሴ ለኔ (፪x) ሰው ሁሉ ይሄዳል ወደየ አምላኩ ስዓቱ ሲያበቃ የዚች ዓለም ልኩ ለእኔ ግን አንተው ነህ የነፍሴ ውሳኔ ከኃጢአት ያዳንከኝ ኢየሱስ መድህኔ(፪) አዝ መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ እየሱሴ ለኔ (፪x) በጓዳዬ ያለህ አልማዜ ንብረቴ ለሰው የማሳይህ ትምህክቴ ኩራቴ እውነተኛ ወዳጅ ቀን የማይለውጥህ አነሰብኝ እኔስ እድሜዬን ብሰጥህ(፪) መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ እየሱሴ ለኔ (፪x) እየመሸ ሄደ ፀሐይ ዘቀዘቀች ነፍሴ ግን አሁንም አንተን አለወጠች የዚህ ዓለም ክብር ሃብት ብልጽግና ከአንተ ዓይነጥሏትም ትኖራለች ገና አዝ መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ ኢየሱሴ ለእኔ ለእኔ እየሱሴ ለኔ እየሱሴ ለኔ (፪x)

