Gubae

የኤማሁስ መንገደኞች

Yeiemahus Mengedegnoch

አገኝሁ ይደግ · ኃይለኛ እንዳንተ የለም · 1992

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ የኤማሁስ መንገደኞች አልበም ኃይለኛ እንዳንተ የለም የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና በስፍራችሁ ሆናችሁ ጠብቁት ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል እርሱ ሰብሯችኋልና እርሱ ይጠግናችኋል አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ጠውልጋችሁ ዝላችኋል የምትሉትን አታውቁም ስንፍናና ዝንጉነትን ለምን ከእናንተ አታርቁም እግዚአብሔር እረስቶናል እባካችሁን አትበሉ የሚበዣችሁ ኢየሱስ ታማኝ ነው እኮ ለቃሉ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ይቤዠናል ብለን ነበረ ተስፋ ያደረግነው ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደዚህ ዓይነት አምላክ ነው ስለምን እንደዚህ ትናገራላችሁ ጌታችን ከሞት ተነስቶ አሁን እኮ አለ አብሯችሁ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ስፍራችሁን ለቃችኋል እግዚአብሔር ያላችሁን በሙሉ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ተስፋ እናንተ እንኳን ብትረሱ እግዚአብሔር ግን አይረሳም ከሞት ተነስቷል ንጉሡ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች