Gubae

ዉለታህ እጅግ ብዙ ነው

Wuletah Ejeg Bezu New

አገኝሁ ይደግ · እጣዬ · 2003

ምላሹ ምን ይሆን እግዚአብሔር አብ አንተ ላደረከው አንድያ ልጅህን ስለኛ ብለህ በመስቀል ሞት ተውከው የዕዳውም ጽህፈት ተወግዷል የሚከሰን የለም ልጆችህ ሆነናል ክዚህ ፍቅር የሚለየን የለም ለዘላለም ኧረ እንዴት ልግለጠው እንዴትስ ፍቅርህን ላዚመው ውለታህ ካይምሮ በላይ ነው ኧረ ምኔን ወደድከው ምን አድርጌ ነው የመረጥከኝ ኢየሱስ እባክህ ንገረኝ ውድዬ እባክህ ንገረኝ ኢየሱስ እባክህ ንገረኝ የእሾህ አክሊል ደፍተህ እርቃንህን በቀራንዮ ውለህ ኅጢአት እርግማንን ጉስቁልናን ጥልን ሁሉ ገለህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲያው በነፃ መግባት ሆኖልናል በከበረው ደምህ ከኅጢአት ከሞት ድነናል ዋጅተኸናል ሰዎች ያሞግሱሃል ኢየሱስ ጌታ ይሉሃል ግን ይሄ ላንተ ያንስሃል ሰዎች ይቀኙልሃል ኢየሱስ ጌታ ይሉሃል ግን እኮ መዝሙር ያንስሃል ግን እኮ ላንተ ያንስሃል ግን እኮ ቅኔው ያንስሃል ግን እኮ ዜማው ያንስሃል ግን እኮ ላንተ ያንስሃል ጎልጎታ ዳገት ላይ ተፈፀመ አበሳችን ሁሉ እርሱ ያዳናችሁ ከጨለማ ሃሌሉያ በሉ አመስግኑ የውለታውን ልክ መዝሙራችን አይመጥልንም ከፊቱ እንወድቃለን ልናመልከው አሁንም አሁንም አናቆምም አሁንም አሁንም አናቆምም አሁንም አሁንም አናቋርጥም...... አናቋርጥም ዝም አንልም በገናችን ይደርደር አውታሩም ምስጋናን ይንዘር አዳነን ከወገን ከዘር አዳነን ከነገድ ከዘር አዳነን ከቋንቋ ከዘር በገናችን ይደርደር አውታሩም ምስጋናን ይንዘር ጌትነትህን ይናገር ንጉሥነትህን ይናገር አዳኝነትህን ይናገር ወዳጅነትህን ይናገር

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች