Gubae

ሁሉን ታደርግ ዘንድ

Hulun Taderg Zend

አገኝሁ ይደግ · ብዙ የሆንክልኝ · 2009

አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ ያስጨነቀን ተመታ ሌት ተቀን ያናወጠን በደስታ እንዳናመልክህ በሀዘን ያስቀመጠን አሁን ግን ደስ ብሎናል ከእስራትም ተፈተናል ጌታችን እውነትም ጌታ ድል የአንተ የማታ ማታ ኢየሱስ ብቻህን ጌታ አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ አይሁድ ሁሉ እንዲጠፋ የሞት አዋጅ ታወጀ መርደኪዮስ እንዲሰቀል መስቀያ ተዘጋጀ እጅህ ግን ቀድሞ ደረሰ የሃማ ምክሩ ፈረሰ ወጥመዱ እራሱን ያዘው ሕዝብህን ክብር አለበስከው ባሪያህን ክብር አለበስከው ማነው (፫x) ኃይልህን የሚችለው ማነው (፫x) ግርማህን የሚችለው ኃይልህን የሚችለው ግርማህን የሚችለው (፪x) አለቁ ጠፉ ብሎ ጠላት ወሬ ሲያወራ ሥማችንን ሲያጠፋ ክፉ ዘርን ሲዘራ ሥማችንን አደስክልን ግርማችንን መለስክልን በፊቱ ዘይት ቀባኸን በእጥፍ ፀጋን ሰጠኸን (፪x) ማነው (፫x) ኃይልህን የሚችለው ማነው (፫x) ግርማህን የሚችለው ኃይልህን የሚችለው ግርማህን የሚችለው (፪x) አዝ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ ሃሳብህ አይከለከልም አቤት የእኛ ጌታ ቋጠሮን የምትፈታ አቤት የእኛ ጌታ ጥያቄን የምትመልስ (፪x)

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች