Gubae

አንተው ነህ አቅሜ

Antew Neh Aqemie

አገኝሁ ይደግ · ጨለማዬ በራ · 2012

አመታት አለፉ ዘመናትም ሄዱ እስካሁን በቤቱ አለሁኝ እያገለገልኩኝ/ገና እኖራለሁኝ በቤትህ ተተክዬ እንዳፈራልህ ታማኝ ባሪያ ሆኜ እንድኖርልህ ለኔ ምኞቴ ነው ቀን ከሌት ፀሎቴ በክብር እስክገባ የላይኛው ቤቴ አሜን/*8 እንደዚያች ውርንጫ በላዬ ተቀምጠህ ስራ ስትሰራብኝ ታሪኬን ለውጠህ ይህንን የሰማ ዲያብሎስ ቢቀና ወዴት ያገኘኛል ዛቻው ሁሉ መና አሜን/*4 በድካም በብርታት በመውደቅ መነሳት ከክፉ ውሳኔ ነፍሴን ስትመልሳት ብዙ ጊዜ አየሁህ ጣልቃ ስትገባ ድርሰህ ስታድነኝ ከጠላት ከበባ ያኔ ካንተ ጋራ ጉዞ የጀመሩ አሉ ብዙ ሰዎች ከኋላ የቀሩ እኔ ይገርመኛል እስካሁን መቆሜ ፅዮን እስክገባ አንተው ነህ አቅሜ

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች