አንተን አንተን አለች
Anten Anten Alech
አገኝሁ ይደግ · ብዙ የሆንክልኝ · 2009
ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ አንተን አንተን አለች አልበም ብዙ የሆንክልኝ በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (፪x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (፪x) ከምድረ በዳው ኑሮ ከዛ ከቃጠሎ አንተ ነህ የታደካት ደርሰህላት ቶሎ ስለዚህም ነፍሴ አንተን አንተን አለች ቀንና ሌሊት ፊትህን ፈለገች አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ እውነተኛ ወዳጅ የኑሮ ጣዕሟ ያለ አንተ መኖር አይሆንላትም መጠጊያ ጐጆ ሌላ የላትም አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) ባስለመድከኝ ስፍራ እጠብቅሃለሁ አንተን ካላገኘሁ መቼ እተኛለሁ ሌሊቱ ጭር ብሏል ሰው ሁሉ ተኝቷል ከአንተ ጋር መሆኑ ነፍሴ ግን አምሯታል አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) እግዚአብሔር አለቴ እመካብሃለሁ እስከ ዘለዓለሙ ተስፋ አደርግሃልሁ ምንም ሳትሰራልህ ነፍሴን ወደሃታል ለቀሪውስ ጉዞ ምንድን ያሰጋታል በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (፪x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (፬x)

